/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ባለፈው ጥር ወር የህወሓት ወታደሮች በንጹሃን ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ በማካሄዳቸው በወልድያ፣ ቆቦ፣ መርሳና ሌሎች አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ይታወሳል።
የደረሱበት የማይታወቅ ሰዎች እንዳሉም ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ብዛት ያላቸው የፖለቲካ እስረኞች ክስ ተመስርቶባቸው በተለያየ እስር ቤቶች ይገኛሉ። ከእስረኞች መካከል የ8 ወር ነፍሰጡር ትገኝበታለች።
ጋዜጠኛ በላይ ማናየ የተወሰኑ የእስረኞችን ስምና ክሳቸውን እንደሚከተለው አቅርቦታል፦
“እስረኞቹ ከወልዲያ፣ መርሳ፣ ቆቦ፣ ሮቢትና አካባቢው ታፍሰው የታሰሩ ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ቀርበው ዋስትና ቢጠይቁም ዋስ መብታቸው ተነፍጎ በእስር ላይ ናቸው። ከመርሳ ከተማ የታሰሩ በርካቶች ዛሬ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወልዲያ ምድብ ቀርበው ነበር። እስረኞቹ በህዝባዊ ተቃውሞው ወቅት “ወያኔ ሌባ፣ በወያኔ አንገዛም በማለት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ንግግሮች አድርገዋል” የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ተገልፁዋል።
ከእስረኞቹ መካከል መርሳ ከተማ ላይ የታሰሩና በአንድ መዝገብ የተካተቱት የሚከተሉት ናቸው።
1, ኃይሉ አስፋው
2, ጌታቸው አባይ
3, ደምሴ ክብረት
4, አያሌው ፀጋዬ
5, ሰማው መንገሻ
6, ወርቅነሽ መንገሻ (የ5ኛ ተከሳሽ እህት)
7, ንጋቱ አየነው
8, ተስፋዬ ካሳዬ
9, ቢኒያም አለሙ
10, ሰይድ አያሌው
11, ኤፍሬም፣ …. ናቸው።
በሌሎች ከተሞችም ሆነ በመርሳ ያለው የታሳሪዎች ቁጥር በርካታ መሆኑ ታውቋል።”