ግዕዝን ሲያልም የሞተው ደራሲ ጆርጅ በርናንድ ሿው /ሰይፉ ኣዳነች ብሻው/

ግዕዝን ሲያልም የሞተው ደራሲ ጆርጅ በርናንድ ሿው /ሰይፉ ኣዳነች ብሻው/

ደራሲው ጆርጅ በርናንድ ሿው ግዕዝን አውቆ ቢኾን ኖሮ
ላቲን ቦታ አይኖረውም ነበር። የላቲንን ድክመት ተጠቃሚዎቹ ራሳቸው በሚገባ ያውቁታል። አዲስ መፍትኄ እንዲገኝለት ይወተውቱና ሰለ ድክመቱ ይበሣጩ ከነበሩት መካከል አንዱ ታዋቂው አየርላንዳዊ የሥነ ጽሑፍ ሰው አቶ በርናንድ ሿው ነበር። በርናንድ ሿው ከ1926 እስከ 1939 የቢቢሲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አማካሪ ኾኖ ለ13 ዓመት አገልግሏል።

ጆርጅ በርባንድ ሿው የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲሻሻል በብዙ የጣረ ሰው ነበር። በዚኽም የተነሣ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርቧል። በብረት ቀጥቃጮች ዘንድ የሌለ ‘እጄን አመመኝ’ አቤቱታ በጸሓፊዎች ዘንድ የበዛው ደነዞቹን ኆኄያት ተነባቢ የሚያደርጉት አናባቢዎች ቃላቱ ለአረፍተነገር ከመድረሳቸው በፊት ትርጕም እንዲሠጡ የሚገቡት ትርፍ ኆኄያት የእጅ እንቅስቃሴ ላይ (Writers’ cramp) ጉዳት በማስከተላቸው ነው። ይኽ አንዱ ችግር ሲኾን የአናባቢዎቹ ሥርዓትና ትርጕም የለሽነት ውጥንቅጥ ግራ የሚያጋባ በመኾኑ የተሻለ ዘዴ ሊፈለግለት ይገባል ባይ ነበር አቶ በርናንድ።

ደራሲው ጆርጅ በርናንድ ሿው Pygmalion, በተሠኘው ቃለ ተውኔትቱ መግቢያ ላይ የሚከተለውን አስነብቧል።
“The English have no respect for their language, and will not teach their children to speak it. They cannot spell it because they have nothing to spell it with but an old foreign alphabet of which only the consonants – and not all of them – have any agreed speech value. Consequently no man can teach himself what it should sound like from reading it … (ሠረዝ የራሴ)

በርባንድ ሿው በጥናታዊ ጽሑፉ ገፅ 26 ላይ እንደገለፀው ላቲኑ የቃላት ምጣኔ ቢኖረው ኖሮ (የአናባቢዎቹ ድግግሞሽን ማለቱ ነው) በነበረኝ የረጅም ዘመን የሥነ ጽሑፍ ሙያዬ በእያንዳንዱ በጻፍኳቸው አንድ ሺህ ቃላት ግማሹን አተርፍ ነበር። የአገልግሎት ዘመኔም በእጥፍ የጨመረ ይኾን ነበር ብሏል። ይኽም የሌሎች የሥነ ጽሑፍ ሰዎችን ሥራ ሲጨምር ምን ያህል ትርፋማ ሊኾን እንደሚችል ግምቱን አስፍሯል። ይኽ ብቻ አይደለም የማተሚያ መሣሪያዎች እገልግሎት እድሜ፤ የወረቀት ውጤቶችን ጨምሮ ሊገኝ ስለሚችለው ጥቅም ገልጿል። ላቲኑ ሊሻሻል ቢችል የነበረውን ተስፋም በጥናታዊ ጽሑፉ እንዲኽ ሲል ገልፆታል።

“With a new English alphabet replacing the old Semitic one with its added Latin vowels I should be able to spell t-h-o-u-g-h with two letters, s-h-o-u-l-d with three, and e-n-o-u-g-h with four: (ልክ እንደ ግዕዙ ማለቱ ነው) nine letters instead of eighteen: a saving of a hundred per cent of my time and my typist’s time and the printer’s time, to say nothing of the saving in paper and wear and tear of machinery.” ይልና በገፅ 35 ላይ ደግሞ እንደዚኽ ይላል “My concern here, however, is not with pronunciation but with the saving of time wasted. We try to extend our alphabet by writing two letters instead of one; but we make a mess of this device.”

ላቲኑ መሻሻል ወይንም በአዲስ መተካት ዐለበት ብሎ ያመነው በርናንድ ሿው የተመኘው ለውጥ ቢመጣ ስለ ነበረው ሥጋትና ያለውን ምርጫ በገፅ 45ና 47 የጥናት ትንታኔው ላይ እንዲኽ ሲል ይገልፀዋል። (45)”The only danger I can foresee in the establishment of an English alphabet is the danger of civil war. Our present spelling is incapable of indicating the sounds of our words and does not pretend to; but the new spelling would prescribe an official pronunciation. (47) Still, we must take that risk. If the introduction of an English alphabet for the English language costs a civil war, or even, as the introduction of summer time did, a world war, I shall not grudge it. The waste of war is negligible in comparison to the daily waste of trying to communicate with one another in English through an alphabet with sixteen letters missing. That must be remedied, come what may.

ደራሲው በገፅ 47 ላይ እንደገለፀው እንግሊዝኛ ምን ያህል በላቲኑ እንደተበደለና ለውጥ እንደሚያስፈልገው ለውጥ ቢመጣ የእርስ በእርስ ወይንም የዓለም ጦርነት ቢነሣ እንኳን ተገቢ እንደኾነ ያለውን እምነት ነበር ያሣየው። ታዲያ በቋንቋው የተካነውና በዓለም ደረጃ ታዋቂነት ላለው ቢቢሲ ለቋንቋ እርምት 13 ዓመት ያገለገለው ባለሙያ የላቲኑ ድክመት ተለውጦ እንኳን ዓለም ጦሩን ቢሠብቅ ጉዳይ አይሠጠኝም እንዳለ እየታወቀ ኦሮሚኛ ከእንግሊዝኛው በበለጠ አናባቢዎችን እያደራረበ ለመሥራት መምረጡ በወጪ እና በቁስ ምን ያህል ጉዳት እንዳለው ቁቤን መጠቀም ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ያለውን በማጤን እርማት ማድረግ አስፈላጊ ነው። ደራሲዎችና አስተዳደሮች ከወጪ አኳያ እንኳን ቢመዝኑት ትርፍ ያለውን ግዕዝ መጠቀሙ እጅግ የሚያዋጣ ነው። በርናንድ ሿው ሰለ ግዕዝ አውቆ ቢኾን ኖሮ ችግሩ ይቃለልለት ነበር። ምክንያቱም ይመኘው የነበረውን አሟልቶ የሚገኘው ግዕዝ በመኾኑ።

በርናንድ ሿው እንዲኽም ሲል ተመኝቶ ነበር፣ “I want our type designers, or artist-calligraphers, or whatever they call themselves, to design an alphabet capable of representing the sounds of the following string of nonsense quite unequivocally without using two letters to represent one sound or making the same letter represent different sounds by diacritical marks. The rule is to be One Sound One Letter, with every letter unmistakably different from all the others. Here is the string of nonsense. An alphabet which will spell it under these conditions will spell any English word well enough to begin with. .. As well as I can count, this sample of English contains 372 sounds, and as spelt above requires 504 letters to print it, the loss in paper, ink, wear and tear of machinery, compositors’ time, machinists’ time, and author’s time being over ~6 £ (amount did not scan), which could be saved by the use of the alphabet I ask for. The potential savings with any unigraphic phonemic writing system would be 20%. [400 letters instead of 500].

ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ደራሲው እዚኽ ላይ ያነሣው ልዩ ነገር ዐለ። እኛ እንግሊዝኛ 26 መነሻ ኆኀያት ስላሉት ቀላልና የተሻለ አድርገን እንገምታለን። የእኛ የፊደል ገበታ ከ”ሀ-ፐ” ርቢዎቹን ከዲቃላዎቹ ጋርን ጨምሮ ቍጥራቸው በርካታ ቢመስሉንም እንግሊዝኛ ተሻሽሎ ሲቀርብ ልክ እንደ ግዕዛችን የፊደል ገበታ ላይ ቢነጠፍ 372 እንዳለ ግን 504 ድምፆችን በማውጠት የሚነገር ቋንቋ ነው። ይኽ ብቻ አይደለም 26ቱ የላቲን ኆኀያት ለአንድ ቋንቋ ተገቢ የኾኑትን ድምፆች መግለፅ እንደማይችል በርናንድ ሿው እንግሊዝኛው በጽሑፉ ገፅ 47 ላይ “… trying to communicate with one another in English through an alphabet with sixteen letters missing.” በማለት የላቲኑን ችግር ይገልፃል። የዚኽ አመልካችነቱ ተሸናፊው ላቲኑ ብቻ ሣይኾን ላቲን አምላኪዎችም ጭምር መኾኑን ነው።

“English spelling can present problems for writers, even for those who are born into English-speaking cultures. There are a number of letters in English that are not pronounced or pronounced differently in certain words. This pattern of irregularity affects about 25% of English words, but within that 25% are about 400 of the most frequently used words.”
የላቲንን ድክመት ካወቀው ደራሲዎች መካከል ዊሊያም ሸክስፒርም ስሙን በተለያየ መንገድ ይጽፍ ሰለ ነበር በላቲን አፃፃፍ ደስተኛ እንዳልነበረም ይነገራል። ስለዚኽ ግዕዝ ላቲንን ተክቶ መሥራት የሚችል አስተማማኝ ፊደል ነው። ጆርጅ በርናንድ ሿው ግዕዝ አውቆ ቢኾን ኖሮ ላቲን ቦታ አይኖረውም ነበር።

የጆርጅ በርናንድ ሿውን ጥናታዊ ጽሑፍ በዚኽ ማስፈንጠሪያ ሊያገኙት ይችላሉ።
http://www.digitalcomposition.org/essays-and-articles/george-bernard-shaw

 

 

981039D0-123D-4C6B-969F-78B7428C73B9

የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር
ሚንስትር ሠርጂዬ ላቭሮቭ
በባለ ግዕዙ ክራቫት አጊጠው

1 COMMENT

  1. በርካታ ምሁራንና አክቲቪስቶች ለአቶ ለማ መገርሳ ደብዳቤ ጻፉ – በኦሮሚያ ኣማርኛ የሥራ ቋንቋ እንዲሆንና የሌሎች ማህበረሰባት መብት እንዲጠበቅ በመጠየቅ |

    […] ነበር የሚል ጽሑፍ በሰይፉ ኣዳነች ቢሻው እዚህ ቀርቧል። [930] የላቲን ፊደል ለእየኣንድኣንዱ ድምጽ ኣንድ ቀለም […]

LEAVE A REPLY