/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ ትላንት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ቤት የምስጋናና የሽልማት ስነስርአት የተደረገላቸው በቅርብ የተፈቱ እስርኞች በድጋሚ ከታሰሩ ብኋላ እስካሁን አለመለቀቃቸው ታወቀ፡፡ እስረኞቹ እስካሁን አልተፈቱም፤ ወልደያ ለምን ሄዳችሁ ተብለው ተጠይቀዋል፡፡
ትላንት ወደ እስር ቤት በድጋሚ የተጣሉት እስረኞች በጠባብ ክፍል ውስጥ በርካታ እስረኞች ጋር ሆነው ከመታሸጋቸውም በላይ በወገቡ ህመም ምክንያት ትንሽ መተኛት ከቻለው ጋዜጠኛ ተመስገን ውጭ የእስር ቤት አዳራቸው አስቸጋሪ እንደነበርና ቆመው ማደራቸው ታውቋል፡፡ በአንጻሩ ማህሌት ፋንታሁንና ወይንሸት ሞላ ጋደም የሚሉበት ቦታ አግኝተው እንደነበር የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ አስታውቋል፡፡
ኮከብ የሌለውን ባንዲራ ግብዣ በተደረገበት ቦታ ሰቅላችኋል በሚል ፖሊስ ቃላቸውን እንደተቀበላቸው ለቪኦኤ አማርኛው ዝግጅት ክፍል የተናገሩ ሲሆን ይህ እንደምክንያት ይነሳ እንጂ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፋችኋል በሚል ሊከሰሱ እንደሚችሉ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል፡፡
ለምን ወደ ወልደያ ሄዳችሁ ተብለው የተጠየቁት የፖለቲካ እስረኞች በሞባይል ስልካችሁ ዋና ገጽ ላይ አረንጓዴ፡ ቢጫ፡ ቀይ ያለበትን የኢትዮጵያ ባንዲራ አድርጋችኋል በሚል ከተከሰሱ ሌሎች እስረኞች ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ እና ሌሎች ከኦሮሚያ ክልል የመጡ 70 የሚሆኑ እስረኞችም በጠባቧ ክፍል ውስጥ ታፍገው እንደዳደሩ ታውቋል፡፡
በአሁኑ ሰአት ጎተራ ወይንም ፔፕሲ በመባል ቦታ እንደሚገኙ ታሪኩ ደሳለኝ በማህበራዊ ድረ ገጾች ይፋ አድርጓል፡፡ ትላንት ወደ እስር የተወሰዱት እስረኞች አስራ አንድ ሲሆኑ እውቁን ጋዜጠኛና የሰባዊ መብት ተሟጋች የሆነው እስክንድር ነጋንና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጭምሮ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራር የነበረው አንዷለም አራጌ፡
የዞን ዘጠኞቹ ማህሌት ፋንታሁንና በፍቃዱ ሀይሉ
የቀድሞ ሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላ እንዲሁም
ዘላለም ወርቅአገኘሁ
ይድነቃቸው አዲስ
አዲሱ ጌታነ
ተፈራ ተስፋዬ
ስንታየሁ ችኮል እንደሚገኙበት ለመረዳት ተችሏል፡፡