40 አለም ዓቀፍ የሲቪል ማህበራት ለዶክተር አብይ አህመድ የአቤቱታ ደብዳቤ ጻፉ

40 አለም ዓቀፍ የሲቪል ማህበራት ለዶክተር አብይ አህመድ የአቤቱታ ደብዳቤ ጻፉ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከቁጥራቸው 40 የሚሆኑ አለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች በሚቀጥለው ሰኞ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቃለ መሀላ ይፈፅማሉ ተብሎ ለሚጠበቁት ዶክተር አብይ አህመድ የአቤቱታ ደብዳቤ ጻፉ።የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ደብዳቤ በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ የታሰሩት ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የሚጠይቅ ነው።

እ.ኤ.አ መጋቢት 25/2018 በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤት ሻይ ቡና እያሉ በፖሊስ የተያዙት እነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጾ፤ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የፖለቲካ አክቲቪስቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የሲቪል ማህበራት ድርጅቶቹ በደብዳባቸው በርካታ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን የሚከተሉትን ሦስት መሰረታዊ ጉዳዮችን የኢትዮጵያ “መንግስት” እንዲከውን አስገንዝበዋል።

(1) ሁሉንም ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱና ህጋዊ መብቶቻቸውን የመጠቀም፣ የመሰብሰብ፣ ሀሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት መብቶቻቸው እንዲከበሩ፤

(2) በጋዜጠኞችና በዜጎች ላይ የሚፈጸመው መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰት እንዲያበቃና

(3) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ የመብት ድንጋጌዎችን በሚያከብር መልኩ እንዲሻሻልና እንዲከለስ ጠይቀዋል።

ፔን ኢንተርናሽናል፣ፍሪደም ሀውስ፣አርቲክል19፣ሪፖርተር ዊዝ አውት ቦርደርስና ሌሎችም ይገኙበታል።

LEAVE A REPLY