የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በእስር ላይ የሚገኙትን ግለሰቦች ቁጥር ይፋ አደረገ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በእስር ላይ የሚገኙትን ግለሰቦች ቁጥር ይፋ አደረገ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከየካቲት 9/2010ዓ.ም ጀምሮ ለሁለተኛ ጊዜ የታወጀው እና በፓርላማ ቁጥር ተጭበርብሮ ስራ ላይ በዋለው “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” ሰበብ በርካታ ንፁሃን ዜጎች እየታሰሩ፣ እየተገደሉና እየተሰደዱ ነው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድ ተብሎ የተቋቋመው አካል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስካሁን በመላ ሀገሪቱ ከ1107 ሰዎች በላይ በኮማንድ ፖስቱ መታሰራቸውን አስታውቋል።

የታሩት ሰዎች የተጠረጠሩበት ወንጀልም በግድያ፣ ቤት ማቃጠል፣ የመንግስትና የግለሰቦችን ንብረት ማውደም፣ በመንገድ በመዝጋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቶችን በማስተጓጎል፣ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መግታት፣ ጎሳን ከጎሳ (ብሄርን ከብሄር) በማጋጨትና በሌሎች ወንጀሎችም እንደተጠረጠሩ የቦርዱ ሰብሳቢ ገልጸዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰሩትን ሰዎች

ቀጠና 1 – (አዲስ አበባ)=450

ቀጠና 2 – (ሀዋሳ ወይም አዳማ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ አርሲ ባሌና ሮቤ ከተማ)=39

ቀጠና 3 – (ድሬዳዋና ሐረር)=178

ቀጠና 4 – (ጅማና ነቀምት)=388

ቀጠና 5 – (ባህር ዳር)=43

ቀጠና 6 – (ሰመራ)=9

ጠቅላላ ድምር 1107 ሰዎች መታሰራቸውን ገልጿል።

LEAVE A REPLY