/ኢትዮጵያ ነገ/፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት አዲግራት ላይ ሲካሄድ የነበረው የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና መቀሌ ከተማ ጨዋታ በደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ አለመካሄዱ ይታወቃል።
ትናንት በረፍት ሰዓት በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የተቋረጠው ጨዋታ ዛሬ 04:30 ላይ የሁለተኛ አጋማሽ ጫዋታውን በወልዋሎ ስታድየም ለማካሄድ መርሀ ግብር ቢወጣም “ኮማንድ ፖስቱ” ጨዋታው እንዳይካሄድ ትዕዛዝ በማስተላለፉ ጫወታው ሳይካሄድ መቅረቱ ታውቋል።
መቀሌ ከተማና አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ቡድኖች ከዚህ ቀደምም ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲጫወቱ ግልጽ የሆነ የዲሲፒሊን ግድፈት ሲፈጽሙ መቆየታቸው የሚታወቅ ሲሆን ለአብነትም ከፋሲል ከነማ፣ ከወልዲያ፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ ሀዋሳ ከነማና ከሌሎች ቡድኖች ጋርም ባካሄዱት ግጥሚያ ጫወታ እስከማቋረጥ የሚደረስ ረብሻ ማንሳታቸው ይታወሳል።