ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ.ር አብይ አህመድ አንተም ግዴታህን ተወጣ!? …1 /ታሪኩ ደሳለኝ (ሚኪ)/

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ.ር አብይ አህመድ አንተም ግዴታህን ተወጣ!? …1 /ታሪኩ ደሳለኝ (ሚኪ)/

ጠቅላይ ሚንስቴር ይሄ በፍፁም ለመና እንደይመስለህ! በምንም ምክኒያትም ችሮታ እያደረክም እንደሆነም እንዳይሰማህ! በፍፁምም መልካም ነገር እንደምትፈፅም እንዳትቆጥረው ጠቅላይ ሚንስቴር ግዴታህን ነው የማስታውስህ።

ዛሬ ከተሾምክ የመጀመሪያ ለሊትህ በቤተ-መንግስት ተኘተህ እያሳለፍክ ነው በዚህ ሰአት ደግሞ ብዙሀን ለሃይ ሰባት አመታት እንዳደረጉት ዛሬም እናትና አባት፣ እህትና ወንድም፣ሚስትና ልጆች፣ አብሮ አደግ ጓደኛና እጮኛ፣ ዘመድ አዝማድ እና ጉረቤት የቅይው ሰው አሁንም በግፍ እየተገደሉ ላሉት ልጆቹ እና ወገኖቹ እንባውን እያፈሰሰ እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር ከነጋት እስከ ነጋት በህዘን ተሰብሮ ዛሬም ተቀምጧል።

በርካታዎች ለሃይ ሰባት አመት እንዳደረጉት ዛሬም እኛና እኛን መሰሎቹ ኢትዮጵያን ከፊት በማድረጋቸው ብቻ በግፍ ለታሰሩብን ቤተሰቦቻችን ስንቅ ለመቋጠር ሳንተኛ ነቅተናል።

በርካታዎች ለሃያ ሰባት አመታት በሀገራቸው መኖር ስላልቻሉ ዛሬም የብርሃው አሸዋ እየወጣቸው እንደመሸባቸው እየቀሩ ነው።

በርካታዎች በግድ ከሀገራቸው እንዲወጡ ተደርገው በያሉበት ሀገራት እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ዛሬም የኢትዮጵያ ፍቅር እያስባነናቸው ሳይተኙ ያነጋሉ።

በርካታዎች በሞያቸው በዕውቀቱ ሳያንሱ በአድሎ እንዳይሰሩ ተደርገው የተቀመጡ ወጣቶች ለማያገኙት ስራ ዛሬም በኢትዮጵያቸው ጉዳና ላይ ሊኳትኑ ሳይተኙ አድረዋል።

ዛሬም አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ሁሉንም መብቱን ተነጥቆ ተቀምጧል። ለምን ያለውም እየተገደለ፣ እየታሰረና እንዲሰደድ እየተደረገ ለሃያ ሰባት አመታት ቆይቶል። ግድያ፣እስሩና እንግልቱ ግን ለምን ብሎ የሚሞግት ሰውን እንዳይኖር አለደረገው ይልቅም ይበልጥ ለሀገሩና ለአቋሙ እስከ ቀራኒዮ ሊሄድ የቆረጠ ትውልድ ተፈጠረ እንጂ።

ጠቅላይ ሚንስቴር እኛ ትላንት በፓራማ ኢትዮጵያ እያልክ ስሞን ደጋግመህ ለጠራሀት ሀገራችን እየወደቁ ያቆዩልን እየሞቱ ያኖሩልን እየታሰሩ እየተንገላቱ ለትንሰኤዎ ያጎነበሱ ቤተሰቦች ልጆች ነን። ያለአድሎ በችሎታው የሚሰራ፣ በሻው ሰአት ወጥቶ ገብቶ የሚኖር፣ ሲወለድ የተሰጠው ነፃነት የሚከበርለት፣ ሃሳቡን በነፃነት እንዲገልፅ የማይገደብ፣ሁሉም በሀገሩ በኩል የሚታይበት፣ ለሚያሰብ ሰው እስር ቤት የማይኖርበት ኢትዮጵያ እንድትኖር ስለምንፈልግ እኛም ሰዋዊ መብታችንን እንተገብራለን እንጆ አንጠይቅም። ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ.ር አብይ አህመድ ያለህ ምርጫ እርሱ ነው እና አንተም በበኩልህ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ግዴታህን እንድትወጣ እጠይቅሀለሁ!?

ታሪኩ ደሳለኝ (ሚኪ)
መጋቢት 24/2010 ዓም ለሊት ለመጋቢት25/2010 ዓም አጥቢያ

LEAVE A REPLY