/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከመጋቢት 16 ቀን ጀምሮ ላለፉት 11 ቀናት በእስር የቆዩት 11 እስረኞች ዛሬ ተለቀው ማምሻውን በመጀመሪያ ታስረውበት ከነበረው የእነ ተመስገን ደሰለኝ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት አምሽተዋል።
ከአስር መፈታታቸውን ምክንያት በማድረግ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት በተደረገላቸው የምስጋና ምሳ እና የሽልማት ስነስርአት ላይ በድንገት በታጣቂዎች ተከበው የተያዙት እስረኞች ኮከብ አልባ ባንዲራ ሰቅላችኋል በማለት ፖሊሶች ወደእስር ቤት የወሰዷቸው ጋዜጠኞች ጦማሪያንና የፖለቲካ አመራሮች በተደጋጋሚ ይፈታሉ በሚል ሰሞኑን ሲጠበቅ ነበረ።
ዛሬ የተለቀቁት እነዚሁ እስረኞች በእስር ላይ የነበሩት ወቅት ክሳቸው እየተቀያየረ አንድ ጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሌላ ጊዜ በአካባቢው ፖሊሶች ነወ የተያዙት ሰበለ የነበሩ ሲሆን ባንዲራውን ማነው የሰቀለዉ በማለት በፖሊሶች ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ሁላችንም አንድ ላይ ነው የሰቀልነዉ ማለት ኃላፊነት ወስደው እንደነበር ይታወቃል።
ከተፈች እስረኞች ውስጥ ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ እና ተመስገን ደሳለኝ፣ ፖለከኛው አቶ አንዷዓለም አራጌ እንዲሁም ወይንሸት ሞላ፤ ጦማሪያኑ በፍቃዱ ኃይሉ እና ማኅሌት ፋንታሁን ይገኙበታል።