/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በኢትዮጵያ ከአምስት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት በአብኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ዛሬ መለቀቁ ታወቀ።
አዲስ አበባን ሳይጨምር በመላ ሀገሪቱ የሞይል ዳታ ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን የዋይ ፋይ ኢንተርኔትም ከአንዳንድ ከተሞች በስተቀር ተቋርጦ ቆይቷል።
በኢትዮጵያ የተጀመረውን የህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የህወሓት/ኢህአዴግ የአገዛዝ ቡድን ህዝቡ መረጃ እንዳይለዋወጥ ለማድረግ የሶሻል ማዲያዎችንና በውጭ ሀገር የሚተላለፉ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ሲያፍን ቆይቷል።
በኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎች የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በተለይም ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የኢንተርኔት መቆራረጥ እየተለመደ መጥቷል። ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አግልግሎትን ስትዘጋ በየ ወሩ እስከ 9.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደምታጣ በዘርፉ የተሰማሩ አለም አቀፍ ተቋማት ይጠቁማሉ።