የዋልድባ መነኮሳት ክስ መቋረጡ ተገለጸ

የዋልድባ መነኮሳት ክስ መቋረጡ ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የዋልድባ መነኮሳት አባ ገ/የሱስ ኪዳነማርያምና አባ ገ/ስላሴ ወልደ ሀይማኖትን ጨምሮ 114 የፖለቲካ እስረኞች ክሳቸው መቋረጡ ተገለጸ። የመንግስት አፈ-ቀላጤ የሆነው “ዋልታ” እንዘገበው ሁለቱ መነኮሳትና ሁሉም ክሳቸው የተቋረጠላቸው እስረኞች ይፈታሉ መባሉን ዘግቧል።

በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል ላቀው ክስ መዝገብ ስር ከተከሰሱ 35 ግለሰቦች መካከል አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም ካሴ (4ኛ ተከሳሽ) እንዲሁም አባ ገ/ስላሴ ወ/ሀይማኖት (5ኛ ተከሳሽ) ነበሩ።

በ2008ዓ.ም ጎንደር በነበረው ህዝባዊ ንቅናቄ ወቅት ተሳትፈዋል ተብለው መንግስት ይፈልጋቸው የነበሩ ግለሰቦችን መንግስት እንዳይዛቸው ከለላ ሰጥተዋል በማለትና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል በ“ሽብር ወንጀል” ተከሰው የነበሩት ሁለት የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ከሁለት ዓመታት በላይ ከፍተኛ ሰቆቃ እንደተፈጸመባቸው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY