በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ የተፈፀመው ግፍ በከፊል /በላይ ማናዬ/

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ የተፈፀመው ግፍ በከፊል /በላይ ማናዬ/

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ወልዲያ ከተማ ጥር 2010 የጥምቀት በዓል ላይ ተቀስቅሶ ወደተለያዩ የአካባቢው ከተሞች ተስፋፍቶ ሲካሄድ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በርካቶች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ሌሎች ደግሞ እስር ቤት ተግዘዋል። ከባድ ድብደባ የተፈፀመባቸውም አያሌ ናቸው።

በወቅቱ በተለያዩ ከተሞችና አቅራቢያቸው (ወልዲያ፣ መርሳ፣ ቆቦ፣ ሮቢት፣ ሲሪንቃ) ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል። በእነዚህ አካባቢዎች በወቅቱ የተፈፀሙ ግፎችን ለማጣራት ሞክሪያለሁ። ሆኖም እዚህ የተገኙት መረጃዎች በግል ጥረት የተገኙና የግፉን ደረጃ ሙሉውን የማያመለክቱ መሆናቸውን ለመግለፅ እፈልጋለሁ። ምናልባት በተቋም ደረጃ ጉዳዩን ለማጣራት ለሚፈልግ አካል ኮርኳሪ መነሻ ሊሆን ይችላል። በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ በደሎችን የመመዝገብና የማጣራት ስራ ለመስራትም ያነሳሳ ይሆናል።

ወልዲያ

የተገደሉ፣

1, ህፃን ዮሴፍ እሸቱ ተሰማ (ዕድሜ 9 አመት፣ አድራሻ፣፣ ወልዲያ ከተማ)

2, ገብረመስቀል ጌታቸው፣ (አድራሻ፣ ወልዲያ ከተማ)

3, ጋሻው አወቀ (ዕድሜ 31፣ አድራሻ፣ ወልዲያ)

4, ወ/ሮ ዝይን ንጋቴ (እድሜ 65፣ የ6 ልጆች እናትና ልጃቸውን ፍለጋ በወጡበት የተገደሉ) (አድራሻ፣ ወልዲያ)

5, ተማሪ ሻምበል ፍትርስት (እድሜ 18፣ አድራሻ፣ ወልዲያ)

6, ወጣት አሸነፍ ኃይሉ (እድሜ 23፣ አድራሻ፣ ወልዲያ)

7, መምህር ታምሩ በሪሁን፣ (እድሜ 45፣ አድራሻ፣ ወልዲያ)

ቆቦ

የተገደሉ፣

1, ህፃን ዳንኤል ካሳ፣ (ዕድሜ 10 አመት፣ አድራሻ ቆቦ ከተማ፣ ቀበሌ 02)

2, ተማሪ ንጉስ አበበ፣ (ዕድሜ 18 አመት፣ አድራሻ ቆቦ ከተማ፣ቀበሌ፣ 04)

3, አቶ ፈንታ ስጦታ፣ (ዕድሜ 36 አመት፣ አድራሻ ቆቦ ገደመዩ፣ ቀበሌ 040)

ቆቦ እና ሮቢት

ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው፣

1, ተማሪ ሞገስ ደሳለ፣ (ዕድሜ 18 አመት፣ አድራሻ ቆቦ ከተማ፣ ቀበሌ 02) እግሩ ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰበት።

2, ወጣት አድኖ ጌታሁን፣ (ዕድሜ 24 አመት፣ አድራሻ ሮቢት፣ ቀበሌ 01) ታፋው ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰበት።

3, ወጣት በላይ ደሳለኝ፣ (ዕድሜ 22 አመት፣ አድራሻ ሮቢት፣ ቀበሌ 01) ሆዱ ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰበት።

4, አቶ ተስፋዬ መለሰ፣ (ዕድሜ 26 አመት፣ አድራሻ ሮቢት፣ ቀበሌ 01) ጭንቅላቱ ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰበት።

(በወቅቱ ከተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ከሞቱትና ከቆሰሉት በተጨማሪ ፍርድ ቤት ዋስትና ቢፈቅድላቸውም እስካሁን ከእስር ያልተፈቱትን እስክንድር ሞላ እና ንጉስ አበራን ጨምሮ በርካቶች በቆቦ ታስረው ይገኛሉ።)

መርሳ ከተማ

የተገደሉ፣

1, ሰይድ ፍሬው (አድራሻ፣ መርሳ ከተማ፣ ቀበሌ 02)

2, መካነ አያሌው (አድራሻ፣ መርሳ ከተማ፣ ቀበሌ 01)አያሌው

3, ሞላ ብርሃኑ (አድራሻ፣ መርሳ)

4, ምስጋናው (አድራሻ፣ መርሳ)

5, ሙሃመድ አሰፋ (አድራሻ፣ ውርጌሳ)

6, እንድሪስ ሞላ/ አብዱ (አድራሻ፣ መርሳ)

መርሳ ላይ ለእስር የተዳረጉ፣

1, ኃይሉ አስፋው

2, ጌታቸው አባይ

3, ደምሴ ክብረት

4, አያሌው ፀጋዬ

5, ሰማው መንገሻ

6, ወርቅነሽ መንገሻ (የ8 ወር ነፍሰጡር፣ የ5ኛ ተከሳሽ እህት)

7, ንጋቱ አየነው

8, ተስፋዬ ካሳዬ

9, ቢኒያም አለሙ

10, ሰይድ አያሌው

11, ኤፍሬም ወዳይ

12, መንገሻ አሸንፍ

13, ኑረዲን ተገኝ

14, አህመድ ኑሪያ

15, መሰለ ካሳው

16, አበበ ሞላ

17, አሊ መኮንን

18, ሙሃመድ በሸራ

19, መስፍን አያሌው

20, አፈወርቅ ከልክሌ

21, በየነ አሌ

22, ደባስ ክብረት

23, ተስፋው ብርሃኑ

እስረኞቹ በህዝባዊ ተቃውሞው ወቅት “ወያኔ ሌባ፣ በወያኔ አንገዛም በማለት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ንግግሮች አድርገዋል” የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ከታሳሪዎች መካከል ወርቅነሽን ጨምሮ ከሁለት ወራት እስር በኋላ እያንዳንዳቸው ከ5000 -15,000 ብር ዋስትና በማስያዝ ተፈተዋል።

ጉባ ላፍቶ ወረዳ

ከፍተኛ የአካል ጉዳት፣

1, አቶ በላይ አባተ (አድራሻ፣ ጉባ ላፍቶ፣ ቀበሌ 020፣ በድብደባ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶበት፣ የዘር ፍሬው የተጎዳ)

2, ዘላለም አማረ (አድራሻ ወልዲያ፣ ቀበሌ 06፣ እግሩ ከባድ ጉዳት፣ ጭንቅላቱ ላይ ቀላል ጉዳት)

ጉባ ላፍቶ ወረዳ

የገቡበት ያልታወቁ፣

1, ማስሬ ብሬ አስማሚ (ይኖርበት የነበረ አድራሻ፣ ወድመን ቀበሌ 021)

2, በስፋት ብርሃኑ አበበ (ይኖርበት የነበረ አድራሻ፣ ቀበሌ 020)

3, መልሶ ደሳለ ይመር (ይኖርበት የነበረ አድራሻ፣ ቀበሌ 020)

4, በለጠ ጎበና ሲሳይ (ይኖርበት የነበረ አድራሻ፣ ቀበሌ 020)

(ማስታወሻ፣ ይህን መረጃ ለማዘጋጀት ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የጤና ባለሞያ፣ ወንጀል መርማሪ ፖሊስ፣ ጉዳዩን የሚያውቁ የአካባቢው ነዋሪዎችን በምንጭነት አነጋግሬያለሁ።)

LEAVE A REPLY