/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከ12 ጊዜ በላይ በመጥፎነታቸው የሚታወቁት የህወሀት መራሹ መንግስት እስርቤቶች ውስጥ ተጥሎ የነበረውና በቅርቡ ከእስር የተለቀቀው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአመቱ ተሸላሚ ሆነ። ሽልማቱን ለመቀበል በመጭው አርብ ወደ አምስተርዳም ይገባል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በጋዜጦችና ልዩልዩ ድረገጾች ላይ በሚያወጣቸው ጠንካራ ጽሁፎች አገዛዙን በመተቸትና አቅጣጫ በማሳየት የሚታወቅ ሲሆን በእስር በነበረበት ወቅት የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት እና አለማቀፍ የጋዜጠኞች ማህበራት ሽልማቶች ተበረከተዉለታል።
እስክንድር ነጋ በመጪው ጁላይ ወር በሰሜን አሜሪካን የስፖርትና የባሕል አመታዊ ክብረበ በዓል ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ መጋበዙ የታወቀ ሲሆን ከወራት በፊት የኦክስፋም ኖቪፕ አለማቀፍ ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል።