የጠ/ሚትር አብይ አህመድ ሙሉ ካቢኔ አባላት ዝርዝር ታወቀ

የጠ/ሚትር አብይ አህመድ ሙሉ ካቢኔ አባላት ዝርዝር ታወቀ

የቀድሞው ጄኔራል አባዱላ ገመዳ የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር ሆነው ተሹመዋል።

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳዲስና ነባር ሚኒስትሮችን አቅርበው አጸደቁ። ጠ/ሚኒስትሩ ካቀረቧቸው ሚኒስትሮች የቦታ ሽግሽግ ያደረጉና አዳዲስ ሰዎችም ተካተውበታል። የተወሰኑ የቀድሞ ሚኒስትሮች ያልተካተቱ ሲሆን ጌታቸው አምባየ (ጠቅላይ አቃቤ ህግ)፣ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ (የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር) ና ሌሎችም ይገኙበታል። የቦታ ሽግሽግ ካደረጉት መካከል ሲራጅ ፈጌሳ፣ አቶ ሙቱማ መቃሳ ይገኙበታል።

በሌላ በኩል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባለፈው ጥቅምት ወር የመልቀቂያ ጥያቄ ያቀረቡት አባዱላ ገመዳ ተነስተው በምትካቸው ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን ሰይሟል።

ዶክተር አብይ አህመድም ለፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች አዳዲስ ሹመት ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት፦

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሙሉ የካቢኔ አባላት ዝርዝር

1-ደመቀ መኮንን- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2-ወርቅነህ ገበየሁ- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3-ሞቱማ መቃሳ- የመከላከያ ሚኒስትር
4-ታገሰ ጫፎ -የፐብሊክ ሰርቪስና እና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር
5-አብርሃም ተከስተ- የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር
6-ከበደ ጫኔ- የፌዴራል ጉዳዮች እና የአርብቶ አደር አካባቢዎችልማት ሚኒስትር
7-መላኩ አለበል- የንግድ ሚኒስትር
8-ኡባ መሀመድ- የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
9-አምባቸው መኮንን- የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10-ሂሩት ወልደማሪያም- የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
11-ሽፈራሁ ሸጉጤ- የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስትር
12-ጌታሁን መኩሪያ- የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
13-ሲራጅ ፈጌሳ- ትራንስፖርት ሚኒስትር
14-ጃንጥራር አባይ- የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር
15-አይሻ መሐመድ- የግንባታ ሚኒስትር
16-ስለሽ በቀለ- የውሃ፣ መስኖና እና የኤሌክትሪክ ሚኒስትር
17-መለሰ አለሙ- የማዕድን፣ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር
18-ገመዶ ዳሌ- የአካባቢ ጥበቃ፣ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር
19-ጥላዬ ጌቴ- የትምህርት ሚኒስትር
20-ይናገር ደሴ- የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
21-አሚር አማን- የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
22-ተሾመ ቶጋ -የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር
23 ብርሃኑ ፀጋዬ- ጠቅላይ አቃቤ ህግ
24-ፎዚያ አሚን- የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር
25-ያለም ፀጋዬ- የሴቶችና የህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
26-እርስቱ ይርዳው- የወጣትና ስፖርት ሚኒስትር
27-ኡመር ሁሴን -የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን
28 አስመላሽ ወልደስላሴ- በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትየመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር
29- አህመድ ሸዴ- የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር

LEAVE A REPLY