በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። ተማሪዎቹ በዋናው ካምፓስ ዛሬ ጠዋት ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳ፣ ዜጎችን እየገደለ ያለው የመከላከያ ሰራዊትና ፌዴራል ፖሊስ ወደ ካምፓቸው ይመለሱና በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩ ተማሪዎች ይፈቱ የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ታውቋል።

ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸውን ተከትሎ የስርዓቱ ወታደሮች ድብደባን ጨምሮ ብዛት ያለው አስለቃሽ ጭስ ወደ ተማሪዎች መተኮሳቸውም ተገልጿል። ሰላማዊ ሰልፉን አስተባብረዋል የተባሉ ተማሪዎችም መታሰራቸውን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሁለት ሳምንታት በፊትም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን በመያዝ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸው የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY