ዶናልድ ያማሞቶ ከተቃዋሚ መሪዎች ጋር መወያየታቸው ተገለጸ

ዶናልድ ያማሞቶ ከተቃዋሚ መሪዎች ጋር መወያየታቸው ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ዶናልንድ ያማማቶ ከተቃዋሚ መሪዎች ጋር መወያየታቸው ተገለፀ።

ረዳት ሚኒስትሩ ከዶክተር መረራ ጉዲና፣ አንዷለም አራጌ፣ በቀለ ገርባና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ በመገናኘት መምከራቸውን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ገልጿል።

ሐሙስ እለት አዲስ አበባ የገቡት ዶናልድ ያማማቶ ትናንት ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ፣ንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

ዶናልድ ያማማቶ በኤርትራ የሦስት ቀናት፣በጂቡቲ የሁለት ቀናት እንዲሁም በኢትዮጵያ ከሐሙስ ዕለት ጀምረው የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።

ረዳት ሚኒስትሩ ከአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በተገናኙበት ወቅትም በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ እንዲሁም በአሜሪካ ም/ቤት በሙሉ ድምፅ ፀድቆ ለሴኔት በተመራው H.R.128(S.R 168) ዙሪያ ሊወያዩ እንደሚችሉም ይገመታል።

LEAVE A REPLY