የተረጋገጠ የመሬት ይዞታ እያላቸው፣ የመሬት ግብር እየከፈሉ የተባረሩበት ሰበብ አንድ ሰው በመገደሉ ነው። ቀሳውስት የሚያስተምሩት የእግዚያብሔርን ቃል ነው። ከቃሉ ዋነኛው ደግሞ “አትግደል” ነው። ሆኖም ግብር ሲያስከፍላቸው የኖረው የቤንሻንጉል ክልል መንግስት ቀሳውስቱ ለሚቃወሙት ወንጀል በጅምላ ተጠያቂ አደረጋቸው። እናቶችን፣ ህፃናትን፣ ምስኪን ገበሬዎችን በጅምላ እንዳባረረው ቀሳውስትንም አሳደዳቸው። እንደ እግዚያብሔር ፈቃድ ሆኖ ህይወታቸውን ተርፏል።
በምስሉ የሚታዩት ቄስ እንኳሆነ ቸሬ ይባላሉ። በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማሽ ዞን ጅንጋፎይ ወረዳ፣ በለው ደዲሳ ቀበሌ የሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ኃላፊ ነበሩ። በግል ፀብ ምክንያት “ሰው ተገደለ” ተብሎ በጅምላ ከ2000 በላይ ሕዝብ ሲባረር የቅድስ ገብርኤሉን ኃላፊ ቄስም አሳድደዋቸዋል።
ቄስ እንኳሆነ ቼሬ ሜዳ ላይ ከወደቁትና በአሁኑ ወቅት የጤና እክል ከገጠማቸው ተፈናቃዮች መካከል ናቸው። ከቄስ እንኳሆነ በተጨማሪ ሌሎች 14 ቀሳውስትንም አሳድደዋቸዋል። “አትግደል” እያሉ ከሚያስተምሩበት ደብር ከተፈናቀሉት ቀሳውስት መካከል:_
1) ቄስ እንኳሆነ ቼሬ
2)ቄስ ምንአለ አያሌው
3) ቄስ ጎጃም በየነ
4) ቄስ ውበቱ እንየው
5)ቄስ አዲስ አንተነህ
6)ቄስ በለጠ ንጉሴ
7)ቄስ መንክር ውቤ
8ኛ )ቄስ ጫኔ ታደሰ
9) ቄስ ሀብታሙ ሽበሽ
10)ቄስ አደመ መኮንን
11)ቄስ የሽዋስ የኋላው
12)ቄስ ላቀው መንግስቴ
13)ቄስ ስልጣኑ ከፍአለ
14)ቄስ አበበ በእውቀቱ
15)ቄስ አበበ መልሰው ይገኙበታል።
ሌሎች በስም ያልተጠቀሱ ቀሳውስትም እንደተፈናቀሉ ለማወቅ ተችሏል