ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አሜሪካ ሲገባ የጀግና አቀባበል ተደረገለት

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አሜሪካ ሲገባ የጀግና አቀባበል ተደረገለት


/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዛሬ ማምሻውን ዋሽንግተን ዲሲ ዳላስ አየር ማረፊያ ሲደር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በቦታው ተገኝቶ የጀግና አቀባበል ተደርጎለታል።

በአቀባበሉ ስነ-ስርዓቱ ላይ ፖለቲከኞች፣የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች፣ አርቲስቶችና ከተለያዩ የአሜሪካን ግዛቶች የተውጣጡ አድናቂዎቹ መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል። የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ታጋዩ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከረጅም ዓመታት በሗላ ከቤተሰቡና ከአድናቂዎቹ ጋር በሰላም ተገናኝቷል።

0AB0C339-65CD-4309-ADB3-37345AFE1599

እስክንድር ነጋ ወደ አሜሪካ ያመራው መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው አትላንቲክ ካውንስል የተሰኘ ተቋም ባቀረበለት ግብዣ መሆኑን ቀደም ብሎ ተገልጿል። አቶ በቀለ ገርባም የተጋበዙ ሲሆን እርሳቸውም አሜሪካ መግባታቸው ተገልጿል።

አትላንቲክ ካውንስል ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ለአቶ በቀለ ገርባ፣ አንዷለም አራጌና አህመዲን ጀበል በፕሮግራሙ ላይ እንዲገኙለት የጋበዘ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለአቶ አንዷለም አራጌና አህመዲን ጀበል ቪዛ በመከልከሉ ምክንያት ወደ ቦታው ሳያመሩ ቀርተዋል።

LEAVE A REPLY