በኬንያ ግድብ ተደርምሶ በሰውና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ

በኬንያ ግድብ ተደርምሶ በሰውና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በኬንያ ግድብ ተደርምሶ በሰውና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ። ከመዲና ናይሮቢ 190 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው “ናኩሩ ግድብ” ዛሬ ሌሊቱን በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ተደርምሶ ቢያስ 38 ሰዎች ሲሞቱ ከ2500 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የሀገሪቱ የዜና ተቋማት ዘግበዋል።

የኬንያ ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫም የግለሰቦች ንብረትን ጨምሮ ባንኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ጤና ጣቢያዎችና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልጸዋል።

በኬንያ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ምክኒያት በተፈጠረ ጎርፍ ባለፈው ሚያዚያ ወር ብቻ 159 ሰዎች ሲሞቱ ከ260 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY