የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መወያየቱን አስታወቀ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መወያየቱን አስታወቀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኦ.ዴ.ግ)ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መወያየቱን አስታወቀ።

በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው ኦዴግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ወደ ሀገር ቤት የላካቸው የልዑካን ቡድኑ ግንቦት 3 እና 4 /2010ዓ.ም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውይይት ማድረጉን አስታውቋል። ፓርቲው በመግለጫው እንደጠቀሰው “ከኢህአዴግ ጋር ሲወያይ መቆየቱንና ውይይቱንም ለመቋጨት ተጨማሪ የልዑካን ቡድን ወደ ሀገር ቤት እንደሚልክ ጨምሮ ገልጿል።

ኦዴግ በ“ኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ለውጦች እንዲሰፉ፣ እንዲገለብቱና፣ ጥልቀት እንዲኖራቸው” ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። ከኢትዮጵያ መንግስት በኩልም በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ሁሉ ጋር ለመወያየትና ለመደራደር “ዝግጁና ቁርጠኛ” መሆኑን ማረጋገጫ ማግኘቱንም አክሎ ገልጿል።

አቶ ሌንጮ ለታ ከጥቂት ዓመታት በፊት የቀድሞው ድርጅታቸው “የኦሮሞ ነፃነት ግንባር” የኢትዮጵያ መንግስት “በሽብር” ቢፈርጀውም ወደ አዲስ አበባ በማቅናት የእንደራደር ጥያቄ አቅርበው ሳይሳካላቸው ወደ መጡበት ሀገር መመለሳቸው ለብዙዎች ጥያቄን አጭሮ እንደነበር የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY