/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅና አብረዋቸው የነበሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን የፋብሪካው ሰራተኞች ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ሰዎች በተፈፀመባቸው ጥቃት ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።
የዳንጎቴ ሲሚንቶ ዋና ስራ አስኪያጅ ዲፕ ካማራ፣ ፀሀፊያቸውና ሹፌራቸው ጋር በመሆን ከሙገር ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ እያለ ዛሬ ከቀኑ 9፡30 አካባቢ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን መንግስታዊ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በአሁኑ ሰዓት የሟቾችቹ አስከሬን በሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ እንደተወሰደም ተገልጿል።ጸሀፊዋ የአንድ ዓመት ህፃን ልጅን ጨምሮ የሦስት ልጆች እናት እንደነበረች ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።
ናይጀሪያዊው የዳንጎቴ ባለቤ የሆኑት አሊኮ ዳንጎቴ አሁን ማምሻውን በትውተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያመሩና ከፋብሪካው ሰራተኞች ጋር አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ገልጸዋል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን ሙገር ከተማ የሚገኘው የዳንጎቴ ስሚንቶ ፋብሪካ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር አመግባባት እንደነበረና ተሽከርካሪዎቹ በተደጋጋሚ ሲቃጠሉበት መቆየቱ የሚታወስ ነው።