በሳዑዲ አረቢያ ታስረው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከነገ ጀምሮ እንደሚለቀቁ ተገለጸ

በሳዑዲ አረቢያ ታስረው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከነገ ጀምሮ እንደሚለቀቁ ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ በዚያው ታስረው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከነገ ጀምሮ እንደሚለቀቁ ተገለጸ።

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያዊያን እስረኞች እንዲፈቱ ለሳዑዲው ንጉስ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ በነገው እለት አንድ ሺህ እስረኞች እንደሚለቀቁ ታውቋል።

የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ  የሳዑዲ የስራ ጉብኝት  ዋነኛ ዓላማው አድርጎ የነበረው የዜጎች መብትና ከለላ ጉዳይ ጉዳይ ላይ ያተኮረ እንደነበር  የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል።

 በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሳዐዲ አረቢያውን የስራ ጉብኝት በማጠናቀቅ ዛሬ ማምሻውን የተባበሩት አረብ ኢምሬት መግባታቸው ታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሀገር ሲመለሱም ወደ ጋምቤላ ክልል እንደሚያመሩ እየተነገረ ነው።

LEAVE A REPLY