እናት ሐሊማና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶር አቢይ ወግ ! /ነቢዩ ሲራክ ከሳዑዲ...

እናት ሐሊማና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶር አቢይ ወግ ! /ነቢዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ/

 * ለፈጣሪ አምላክ ምስጋና ይድረሰው!

  ብርቱ ናት የምላችላሁ እናት ሐሊማ ለገንዘብ ሰብዕናዋን ሽጣ ለልጇ ፍትህ መከበር ስለ እውነት ቃል እምነቷን ሳታዛንፍ 13 አመት በመከራና ስቃይ ተጓዘች … በ13 ኛው አመት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አቢይን አገኘች …እውነቷን ዘርግፋ አጫውታቸው ፣ ዶር አቢይም “እህ ” ብለው መስማት ያውቃሉና እናት ሐሊማን አዳመጧት !

በመጨረሻም ” አይዞሽ በልጅሽ ጉዳይከልዑላኑ ጋር ተነጋግረናል ፣ አስፈላጊው ካሳችሁ ተከፍሏችሁ በቅርቡ ወደ ሀገር ትገቡ ዘንድ ስምምነት ላይ ተደርሷል ! ” የሚል የደስታ ብስራት እናት ሐሊማን አበሰሯት 🙂 እናማ እናት ሐሊማን ስቃ ፈንድቃ የደስታ እንባ እያጎረፈች ተሳሳምን !

 እናንተ ሰብዕናን ያስቀደማችሁ የብላቴናው አጋሮች ሆይ ድሉ የሁላችሁም ነው ! ምስጋናውም ለእናንተ ነው ! ሀገሬ መሪ አግኝታለች ፣ የዜግነት የላቀ ክብሩ የተሰማኝ ታላቁ አርብ

ጁምአ የፍትህ ዘመቻችን 13 ኛ ሳምንት ስኬት ምክንያቱ ብርቱው የእናት ሐሊማ ጽናትና የእናንተ አጋርነት ነው !

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አቢይ አህመድንና ዶር ወርቅነህን ደጋግሜ አመሰግናለሁ !

ለዚህ ደስ የሚል ቀን ላደረሰን ፈጣሪ አምላክ ምስጋና ይድረሰው !

LEAVE A REPLY