/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ትናንት በስልክ ማነጋገራቸውን የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ገለጸ።
አዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ዶክተር አብይ አህመድ በፓርቲያቸው ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ስለተመረጡ “እንኳን ደስ አለዎት” እንዳሏቸውና የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለሚያደርገው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ አሜሪካ ጠንካራ ድጋፍ እንደምታደርግ ማረጋገጣቸውን ስቴት ዲፓርትመንቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።