ቀጥሎ ያለውን ዘገባ ያገኘሁት ከቃሊቲ ፕሬስ ድረ ገፅ ነው።
ጉዞ ወደ ፊንፊኔ..
አቶ ሌንጮ ለታ(የኦነግ መስራችና ፀሀፊ)የነበሩ
ዶ/ር ዲማ ናጎ(የኦነግ ሊቀመንበር)የነበሩ
ዶ/ር በያን አሶባ(የኦነግ ቃል አቀባይ)የነበሩ
ዶ/ር ሀሰን ሁሴን(የኦነግ አመራር አባል)የነበሩ
አቶ/ሌንጮ ባቲ(የኦነግ ቃል አቀባይ)የነበሩ። የሚል ሲሆን ፦
የእኔ ሃሳብ እና ጥያቄ………….
ወደአገራቸው ስለተመለሱ ደስተኛ ነኝ። ኢትዮጵያ ልጆቿ ሁሉ የሚሰባሰቡባትና የሚኖሩባት፤ በጋራ የሚገነቧት እናም ለልዕልናዋ የሚቆሙላት ልትሆን ይገባል ብዬ አምናለሁ። ከእነ አቶ ሌንጮ በዚህ ወቅት መመለስ ጋር በተያያዘ ስላሉት ፓለቲካዊ ጉዳዮች የተለያየ ምልከታ (ሂደቱ የቆየ እንደሆነም እናስታውሳለን) ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን።
ለዛሬ ግን ወደጎን ሊደረግ ስለማይችለውና በፖለቲካዊ ድርድር ወቅት የተለመደ ስለሆነው የእነሱን ፈር ተከትለው ባደረጉት ጉዞ (አምነውበት ስለመሆኑ ማጠየቅ ሳያስፈልግ) መጨረሻቸው ቃሊቲና ዝዋይ ስለሆነው ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ምን አድርገው ይሆን? የምትመለከቱት ምስል ኢንጂነር መስፍን አበበ ከ12 ዓመት በፊት (በኦነግ አመራርነት ተጠርጥሮና በኬኒያ ፀጥታ ሃይሎች ተባባሪነት ተላልፎ በመሰጠት) ሲታሰርና አሁን ያለው አካላዊ አቋም ነው።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ያስብ፤ ሕዝቧን ይባርክ!