ዶ/ር መረራ ጉዲና አንቀፅ 39 እንዲሻሻል ጠየቁ

ዶ/ር መረራ ጉዲና አንቀፅ 39 እንዲሻሻል ጠየቁ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) ሊቀ-መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና አንቀፅ 39 እንዲሻሻል ጠየቁ።

የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 39  “የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠል” የሚለው  በህዝብ መካከል ላለመግባባት ምክንያት በመሆኑ እንዳሻሻል መጠየቃቸውን ኢትዮጵያን ሄራልድ ዘግቧል።

እንደ ዶክተር መረራ “አንቀፅ 39 በህዝቦች መካክል ከፍተኛ አለመግባባትና ውዝግብን ፈጥሯል፤በመሆኑም በአፋጣኝ ማሻሻያ ሊደረግበት ይገባል ሲሉ በአጽንዖት ተናግረዋል።

ዶክተር መረራ ከዚህ በተጨማሪም ስለ ምርጫ ቦርድ አወቃቀር የሚደነግገው አንቀፅ 102 ሊሻሻልና ራሱን የቻለ ገለልተኛ ቦርድ ሊኖረው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

 

LEAVE A REPLY