በአረብ ሀገራት ያሉት ኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እየአንዳንዳቸው ዜጎቻችውን የጎዱ ናቸው። ዜጎቻቸውን የሸጡ ናቸው። ሁሉም ከዜጋው እንባ አለባቸው። በተለይ ከአምባሳደሮቹ የባሰ ዲፕሎማት ተብለው የሚሄዱ ሰራተኞች ዜጋቸውን እንደ እነሱ ያዋረደ፣ ያስለቀሰ የለም።
በትክክል ዜጋችንን እኛ ስናከብር ነው ሌላውም የሚያከብረው ከተባለ የትኛው የኤምባሲ ሰራተኛ አክብሮ ይምውቃል? አምባሳደሮቹን ብቻ እንደ ካርታ ጨዋታ ፖስቴ ማስመታት ለውጥ አያመጣም። በአረብ ሀገር ላይ ያሉ ዲፕሎማቶች በሙሉ በዘር የተሰገሰጉ እና ከአረብ ጋር ተሞዳሙደው ዜጋቸውን አሳልፈው መስጠት የለመዱ ናቸውና ሁሉም ሊቀየሩ ይገባል። በተለይ ሳዑዲ፣ ኩዌት፣ ዱባይ ቤይሩት ዜጎቻቸውን በመሸጥ ወደር የሌላቸው ከንቱዎች ናቸው።
ዱባይ ያሉ የኤምባሲው ሰራተኞች ላይ አሁን ድረስ የሚሰማው ስሞታ መፍትሄ አላገኘም። ከደላላዎች ጋር ተሞዳሙደው ዜጎቻችንን የሸጡበት ማስረጃ በእያንዳንዱ ዜጋ እጅ አለ። ለውጥ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ እንጂ እንደ አሳ ግማት ለአናት አምባሳደር ውብሸትን መጥራት ከኩዌት ወደ ዳዑዲ ማምጣት ለውጥ አይደለም። ለውጡ ስር ነቀል ይሁን እስኪ ለዜጋቸው የሚሰሩ ዲፕሎማቶች አምጡ….
ዲፕሎማትነት ምን እንደሆነ የማያውቁ ሰዎች ይጽዱ። ከኤምባሲን ግቢ ማንም ተነስቶ ሲደበድብ ተሸማቀው ወተው የሚለምኑ በራሳቸው የማይተማመኑ ዲፕሎማቶች አሰዳቢነታቸው ይብቃ!! ለዜጋቸው የሚያስቡ ሰዎች ሰራተኞች ይኑሩን። አምባሳደር ብቻ መቀየር በቂ አይደለም።..