ለ24 ዓመት በትግራይ የታሰሩት የኦርቶዶክ ተ. ሊቅ እንዲፈቱ አቡነ ኤልሳዕ ለፓትርያርኩ ደብዳቤ...

ለ24 ዓመት በትግራይ የታሰሩት የኦርቶዶክ ተ. ሊቅ እንዲፈቱ አቡነ ኤልሳዕ ለፓትርያርኩ ደብዳቤ ጻፉ

“በጣም የሚገርምና ሚያሳዝን ነገር ነው!”

“ለእኔ ማንም ይሄን ጉዳይ ነግሮኝ አያውቅም!”
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የሊቁ እንደስራቸው አግማሴ ጉዳይ በሚመለከት ብፁዕ አቡነ ኤልሳ ለፓትርያርኩ በጻፉት ደብዳቤ መሠረት የሊቁ የእጎት ልጅ የሆነት ከጎንደር ላይከ ሰላም አለምነውና አዲስ አበባ የሚኖሩት ሌላው ዳመዳቸው አቶ ዋለልኝ ሲሳይ ዛሬ ግንቦት 27 ቀን 2010ዓ.ም ፓትርያርኩን ያናገሯቸውና የሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኾኑት በአቡነ ኤልሳዕ የተጻፈውንም ደብዳቤ በእጃቸው የሰጧቸው ሲሆን በፓትርያርኩ ፕሮቶኮል በኾነው መምህር ሙሴ አማካኝነት የተጻፈው ደብዳቤ ሲነበብም “…ለ24 ዓመት መታሰራቸው ዘጠኝ ልጆች እንዳላቸው” ሲገለፅላቸው በሀዘን እየደጋገሙ “በጣም የሚገርምና የሚያሳዝን ነው” ይሉ ነበር።

በጣም በመተከዝና ግራ በመጋባት “እንዴት ይሄን ያህል አመት በእስር ቆዩ?፤ ምንስ ቢያጠፉ እንዴት እንደዚህ ይደረጋል? በጣም የሚገርምና የሚያሳዝንም ነገር ነው፤ ” ብለዋል።

የመጡትም የሊቁ ቤተሰቦች “አሁን በህይወት አሉበት ስለተባለው ቦታ፤ እሳቸው ከተያዙበት ዕለት ጀምሮ ስለተፈጠረው የቤተሰብ ምስቅልቅል ህይወት አብራርተዋል። ሊቁ እንደስራቸውን ለማግኘት መደረግ ያለበትን የሚሉትን ለፓ ትርያርኩ አቅርበዋል።

ፓትርያርኩም:- “ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ደብዳቤ እንደሚፅፉ፤ በአካልም አግኝተው እንደሚያናግሩት የገለፁ ሲሆን ጉዳዩንም ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚከታተሉት ገልፀዋል።
“ለእኔ ማንም ይሄን ጉዳይ ነግሮኝ አያውቅም! ይሄን ድብዳቤ የጻፉትን ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕም ሊመሰገኑ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ፓትርያርኩ የሊቁን ጉዳይ ሰምተው ማመን እናዳቃታቸው 24 አመት መታሰራውን ሲሰሙ ደንግጠዋል፤ በሀዘንም እራሳቸውን እየነቀነቁ ” ወይ ጉድ” እያሉ ለደቂቃዎች ቆዝመዋል። በተጨማሪም ሀገራቸው ላይ የሚደረገውን ነገር ማወቅ የሚያስችል መረጃ እጥረት እንዳለባቸውና ከመረጃዎች የራቁ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል።

ፓትርያርኩ ጋር የመጡት እንግዶች ያለምንም መጉላላት በአካል ገብተው ያመጡትን ደብዳቤ እንዲያስገቡና በዝርዝር ጉዳያቸውን እንዲያስረዱ ያደረገው

DC03F898-CBFB-4805-8A4E-1C584A69C05C

ECC96028-31E7-4955-B688-E92D3B0FBE26

መንሳዊ_ወንድማችንን ለጊዜው ስም ባልጠቅስም ሌላ ቀን በይፋ ማመስገኔ አይቀርም።

/ከጌታቸው ሽፈራውና ሃብታሙ ምናለ ገፅ የተወሰደ/

LEAVE A REPLY