ከባድመ ጦርነት የተረፈ አንድ ወታደር ጦሩ ኤርትራ ከገባ በኋላ ከመለስ ዜናዊ በተላለፈ ቀጭን ትዕዛዝ ሲመለስ የነበረው ሁኔታ ሲነግረኝ ይዘገንናል። ጦሩ ኤርትራ ሲገባ ምቹ ቦታ ይዞ ነበር። ተመለስ ሲባል ግን ወደ መግደያ ቦታ ገባ። የሻዕቢያ ሰራዊት ተመልሶ መግደያ ቦታ የገባውን ጦር መምታት ጀመረ። በዚህ ወቅት የረገፈው ወታደር በርካታ ነው። ይህ ጦር የረገፈው በመለስ ትዕዛዝ ነው። በጥንቃቄ እንዲመለስ እንኳ ጊዜ አልተሰጠውም።
~መለስ ከዛ በፊትም የጦር አውሮፕላን እንዳይገዛ እንቅፋት ስለፈጠረ የኢትዮጵያ ገበሬ ሲጨፈጨፍ መክረሙን ጓደኞቹ በመፅሀፍ ከትበውታል!
~ ከጦርነቱ በፊት ትህነግ/ህወሓትና ሻዕቢያ በኮንትሮባንድና መሰል ጉዳዮች ይነታረኩ ነበር። በተለይ ገብሩ አስራትና ኢሳያስ ተጣልተው እንደነበር ገብሩ በመፅሃፉ ገልፆታል። አንድ ቀን መለስ ሁለቱን ለማስታረቅ ይጥራል! መቀሌ ላይ! ኢሳያስ ከአስመራ ራሱ መኪና ነድቶ ሲመጣ ሀገሬውን የማያምነው መለስ በሄሊኮፍተር ወደ መቀሌ አቀና። ኢሳያስና ገብሩ ሲከራከሩ መለስ እንደሌላ ሀገር መሪ “አንተም ተው አንተም ተው” ይል ነበር አለ ገብሩ አስራት በመፅሐፉ! መለስ ለኤርትራ ቢከራከር ይቀለዋል!
~መለስ ዜናዊ በ1992 አካባቢ በድብቅ አባይን ለግብፅ አሳልፎ ሰጥቷል!
~የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ሰጥቷል
~ዓለም አቀፍ የህግ ምሁሩ ዶክተር ያዕቆም የአሰብን ጉዳይ እኔ በነፃ ልከራከር ብለው ነበር። ዶክተር ያዕቆም እነዚህን ጥራዝ ነጠቆች በዓለም አቀፍ መድረክ እንደሚያሸንፏቸው ስለሚያውቅ “አልፈልግም” አለ መለስ! ለኤርትራ ቢከራከር ይቀለዋላ! ዶክተር ያዕቆብ በነፃ ልቁም እያሉ እነ መለስ ጉዳዩን የማያውቁት ፈረንጆችን በውድ ጠበቃ አደረገው ቀጠሩ። አደራዳሪዎቹ “አሰብ ለኢትዮጵያ ይገባል” ሲሉ፣ መለስ “ይቅርብን” ብሎ ለኤርትራ ቆመ! የአልጀርስን ስምምነትም ፈረመ! መለስ ስለ ባህር በሩ ሲጠየቅ “ወደብ ሸቀጥ ነው” ብሎ መለሰ። በወደብ አልባነታችን የሸቀጡ ዋጋ ጣራ ነካ።
~የባድመን ጉዳይ የጨረሰው መለስ ነው። የትህነግ ካድሬዎች አብይ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ እየታየ ነው። ባድመን በአለም አቀፍ መድረክ፣ በአደባባይ አሳልፎ ለሰጠው መለስ በየአመቱ የሚያለቅስ ካድሬ አሁን ቡራ ከረዩ ሲል ማለት አስቂኝ ነው! በየ አመቱ ጥቁር ለብሶ እየየ የሚል ካድሬ መለስ ለሰጠው ባድመ አብይ ላይ ሰልፍ ወጣ ሲባል መስማት ቀልድ ነው! ያኔ እነ ስዩም መስፍን ባድመን ሰጥተው ሲመለሱ “አሸንፈናል” አሉ። በመለስ ትዕዛዝ። ተቃዋሚ ሰልፍ ሲወጣ፣ ዛሬ አብይ ባድመን አሳልፎ ሰጠ የሚል ካድሬ የሰልፉ ተቃዋሚ ነበር። ዛሬ መለስ ፈርሞ የሰጠው ባድመ ጉዳይ እንደገና ሲነሳ ሰልፍ! ቢገባቸው ሰልፉ ዛሬ ሳይሆን ያኔ መለስ ሲፈርም መሆን ነበረበት! አሊያም ሲሞት ከማልቀስ ይልቅ “ባድመን አሳልፎ የሰጠው ሞተ” ብሎ የሆነ ስሜቱን መግለፅ ነበረበት! መለስ የፈረመበትን አብይ ምን ያድርግ ተባለ?