የሰሞኑ ዜና /አምባሳደር ዕምሩ ዘለቀ/

የሰሞኑ ዜና /አምባሳደር ዕምሩ ዘለቀ/

ቁጥር ፪ ግንቦት ፪ሺ፲

ጠቅላይ ሚንብትሩ ከተሾመ እነሆ ሁለት ወር አለፈው፡ በዚህ ጊዜ ዉስጥ ጠ/ሚስትሩ ብዙ ተናግሯል ብዙ ቦታ ባገር ዉስጥ ውጪም እየተዘዋወረ ተናግሯል በተለይ የርትግራይን “የኢትዮጵያ ሕዝብ ፋና ሁኖ የበላይ ወርቃማ የተባረከ ልዮ መሪነት ስጦታ” እንዳለው መስክረዋል። ጎረቤት አገሮችንም ጂቡቲን ኬንያንና ሱዳንን ጎብኝተዋል፡ ጋዜጠኞችና አንድ አንድ ስማቸው የታወቀ እስረኞች ተፈተዋል፡ሳዊዲ አረብያ ተጉዞ አል ሙዲንና አንድ ሺ እስረኞች ለማስፈታት ሞክርዋል ፡ አልፎ ትርፎ ንጉሥ እንደሚሆን ይገዛ አናቱ ንግርት እንደሆነ ገልጽዋል፡ የባለስልጣኖች ሹም ሽር አደርግዋል፡ ብዙ የአስተዳደር ቀውሶችና ለዉጦች አሳዉቋል፡ነገር ግን መሰረታዊ የሆኑ ለዉጦች አልተደረጉም፡ ለዚህም ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል ይባላል፡ የተሾሙትም አዲስ ሚኒስትሮች ቦታ ተዘዋወሩ ኢንጂ የቆዩ ባለስልጣን ናችው። አሁንም እዉነተኛዉ ተጨባጭ ሃይል በወያኔዎች እጅ እያለ ጠ/ሚሩ የሚናገረዉና የምያሳየዉ ሃገራዊ አስተያየት ከመረጡት ወገኖች ልማዳዊ አገዛዝና ትግባር በጣም የተለየና ተቃራኒ በመሆኑ ዉጤቱ ምን እንደሚሆን ያጠያይቃል።

በሃግር ዉስጥ የሚካሄደው ሕዝባዊ እምቢታና አመጽ የወያኔዎችን ስልጣን እንዳፈረስዉና እነሱም ተደናግጥዉ ለዉጥ ያመጡ ለመምሰል አዲስ ጠ/ሚር ሾመዉ ህዝቡን እያደናገሩ ስልጣናቸዉን ይዘው ለመቆየት ምሞከራቸው ግልጽ ነው። ነገር ግን በሃገር ዉስጥም ሆነ ብዉጪ በተቃዋሚ በኩል የሚሰማዉ ድምጽና አስተያየት በጣም የበሰለና የሃገርን ሁኔታና ችግር የምያሰፈልገዉንም
መፍተሄ አብራርቶ የሚያስገንዝብ ሆኖ ሳለ፡ እተግባር ላይ ሊያዉለው የሚችል ሃገራዊ ሃይል እስካሁን አልተገኘም። ባሁኑ ውቅት በየፊናዉ የሚወጠነዉ ሰላማዊ እርቅና ድርድር ተመልሶ አዲስ የአምባገነኖች አገዛዝ እንጂ ለሃገሪቷ ሕዝብ መሰረታዊ መብትና ነጻነት ያመጣል ብዬ አላምንም።

በሰፊዉ ሕዝብ በኩል የማያጠራጥር የሃገር ፍቅር እንዳለና፡ ደምና ስቃይ እይተከፈለበት ያለ የሁኔታዉ ግንዛቤ መኖሩና ጠንካራ የለውጥ ፍላጎት እንደመነጨ ግልጽ ነው። ይሁንና፡ ብለፉት አርባ አራት ዓመታት በተለይ በመጨረሻዎቹ ሃያሰባት ዓመት በሕዝቡ ላይ የዋለው የዘረኝነት ጭካኔ ሙስናና ስርቆት አስተዳደር በህብረስቡ ላይ ከባድ በሽታና መቃቃር እንደፈጠረ ግልጽ ነው፡ በአንድ አላማ ተስማምቶ ለመራመድ እንቅፋት ይሆነው ይሄዉ ነው። ስለዚህ ባለፉት ዘመናት በእንደዚህ አይነት ገንዛቤ የወሰዱንን አስተሳሰቦች መመራመርና የማንነታችንን እዉነተያዉን ፍንጭ ማግኘት አለብን።

አሁን እንደሚታየው የወያኔዎች የፖሊቲካ መሰረት ፈርስዋል፡ ስልጣን ከጨበጡ ከ፳ስምንት ዓመት ያተረፉት የመላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥላቻና ንቀት ነው፡ በሕዝቡ ላይ የሰሩት ግፍ ግድያ ጭካኔ አስከመቼም የማይረሳና ለውደፊትም የሚጠየቁበት ነው። ከወልቃይት ጠገዴ ከሰሜን ጎንደር ከአርማጮሆ ከራያ አዘቦት ከወሎ ከቤኒሻንጉል የተወሰድው መሬትና የተፈናቀለው ሕዝብ
ከተወለደበት ከኖረበት ተመልሶ ሃብቱን መልሶ መያዝ አለበት፡ ለሱዳን የተለቀቀው የሃገር መሬት
መመለስ አለበት። ሕዝቡም ለተዘረፈው ለተቀማው ሃብት ካሳ ማግኘት አለበት። የዘረፉትም የሰረቁትም ገንዘብ ተመላሽ ይሆናል። የሚገድፏችውም የዉጪ መንግሥታት ይህንን አዉቀው ሌሎች ወገኖች እያባበሉ ነው። ወገናችን ብለው የሚመኩበት ሰፊዉ የትግራይ ሕዝብ ራሱ አይከተላቸዉም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተገንጥሎ ለመኖር እንደማይችል ያዉቃል። ስለዚህ የወያኔዎቹ አገዛዝ አልቆለታል ለማለት ይቻላል፡ አጥብቆ ማሰብ ያለብን ወደፊት ስለሚሆነው ነው።

በአሁን ወቅት ተዘርግቶ በምናየው ይፖሊቲካ ሰንጠረጅ ላይ ተሰልፈዉ የሚገኙት ዋና ቡድኖች የኦሮሞ ድርጅቶችና የሃዋት አስፈጻሚ ኮሚቴ የሾሙት አዲሱ ጠ/ሚ ናቸዉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከአንድ ሲሶ ከሰላሳ ሚልዮን ይበልጥ የሆነው የአማራው ሕዝብ ስሙ እንኳ አይነሳም፡ ኢንድያዉም በአማራው ላይ የሚካሄደው የግፍ ዘመቻ እየባሰና ጦር እየዘመተበት እየተገደለና እይተሰቃየ ከተወለደበትና ከኖረበት ከየቦታዉ ኢየተፈናቀለ እየተሰደደ ሃብቱን ኢየተቀማ ነው።

ይህ የሆነበት ምክንያት አማራው በራሱ ላይ በፈጠረው ደካማነትና መተማነን ማጣትና ለኢትዮጳያ ሕዝብና ለመጪዉ ትውልድ ያለበትን ታሪካዊ ግዴታና ሃላፊነት ባለማክበርና በመሽⶠ ነው፡አለዝያ ሰላሳ ሚልዮን ሕዝብ ባንድ የወመኔ ሸፍቶች ሰብአዊ መብቱ ተገፎ እንደ እንሰሳ የሚነዳበት መክንያት የለም፡ ይሳፍራል ያሳዝናል። ከአምስት ዓመት በፊት አማራዉ መደረጃት አለበት በዬ ሳስታዉቅ ይህንኑ በማሰብ ነበር።

ያለፈው አልፏል፡ ከአሁን ወዲህ የአማራዉ ሕዝብ ራሱንና አገሩን ኢትዮጵያን ከጥፋት ለማዳን ታጥቆ በአንድነት የመጣዉን አደጋ መመከት አለበት፡ አማራጭ የሌለው ኊኔታ ነው፡ በአገር ቤት ያለው ሕዝብ ይህንን ተረድቷል፡ እንቅፋት የሆኑት የፖሊቲካ ድርጅቶችና ነጋዴዎች ናቸው፡ ፍሬቢስ የሆነ ገበያቸዉን ትተው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንዲሰለፉ እጠይቃለሁ።

የአማራው ሕዝብ በተለይ ወጣቱ ትውልድ “የነገው ሰው” የሆነው አሁን የሚካሄደው የፖሊቲካ ድርድር በእርሱ ዕድል ላይ መሆኑን አጥብቆ መገንዘብ አለበት፡ ድጉንም ክፉንም የሚሸከመው እርሱ ነው፡ በቅርቡ ካለፈው የወረስው መለያየት ዘረኝነትና ጥላቻ ስለሆነ ይህኑን አዉቆ ጥሎ፡ በአዲስ ጤናማ መንፈስንና እዉቀት ኢትዮጵያን መገንባት አለበት።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
እዘ፡

LEAVE A REPLY