/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጄኔራል ሰዓረ መኮንንን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሆነው ተሾሙ። ዛሬ በታላቁ ቤተ-መንግስት በተካሄደው ስነ-ስርዓት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጄኔራል ሰዓረ መኮንንን የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድርገው ሰይመዋል።
የህወሓቱ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በመሆን ላለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮ-ሶማሌና በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎ ለተፈፀሙት የጅምላ ጭፍጨፋ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሆኑት ሳሞራ የኑስ ከሀላፊነታቸው ተሰናብተዋል።
በሌላ በኩል ወታደራዊ ማዕረጋቸው ተገፍፎ ከሰራዊቱ የተባረሩትና ላለፉት 9 ዓመት በግፍ እስር ቤት ያሳለፉት ብ/ጄኔራል አሳምነው ፅጌና ሜ/ጀኔራል አለምሸት ድጋፌ ማዕረጋቸው ከነሙሉ ኮከቡ ተመልሶላቸው እንዲሁም የጡረታ መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መወሰናቸውን የጠ/ሚኒስትር ችፍ ኦፍ ስታፍ የሆኑት አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።