የአማራ ተወላጆችን ያፈናቀሉ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ

የአማራ ተወላጆችን ያፈናቀሉ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አማራዎችን ከኦሮሚያ ክልል ያፈናቀሉ ባለስልጣናት መባረራቸውን የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ድርጅት ጠቁሟል። በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን አፈናቅላችኋል፣ ወይም ለማፈናቀል ሞክራችኋል፣ ጥላቻን ዘርታችኋል፣ ወይም ህዝብ ለህዝብ እንዲጣላ ምክንያት ሆናችኋል የተባሉ የዞን፣ የወረዳ፣ የቀበሌ ና የልዩ ልዩ ቀበሌዎች አመራሮችን አሰናብተዋል፣ የአንዳንዶቹም በህግ እንዲታይ አድርገዋል ብሏል የክልሉ ቴሌቪዥን።

“..የአማራ ህዝቦች ወንድሞቻችን ናቸው፣ ያለ እነሱ እነሱም ያለኛ..ወይም አንዳችን ያለ አንዳችን መኖር አንችልም..በቅርቡ የመጣውን ለውጥ እንኳን ተመልከቱ፣ የሁሉቱ ክልል ህዝቦች ትግል ነው..አሁን የምታዩት ለውጥ ያመጣው… የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች በአማራ ክልል ያለምንም ችግር እየኖሩ ነው፣ ስለሆነም ወንድሞቻችን በኦሮሚያ ክልል ያለምንም ስጋት ሰርተው እራሳቸውን መለወጥ፣ ሀብት ማከማቸት ይችላሉ፣ አንዳንዶች በኦሮሚያ ና በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ አለመተማመንን ለመፍጠር እየተሯሯጡ እንደሆነ በዚህ ሳምንት የታየ ድርጊት መሆኑን አረጋግጫለሁ፣ ስለዚህ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ይንን ሴራ መመከት ያስፈልጋል.. >>..ሲሉ ፕረዚዳንት ለማ መገርሳ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ለማድረግ ሲሞክር አንድ የተደራጀ ቡድን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉትም ተናግረዋል ሲል ነው የዘገበው።

(ትርጉም-ቃሊቲ ፕሬስ)

 

LEAVE A REPLY