የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሦስት ቢሊዮን ዳላር በኢትዮጵያ ለማፍሰስ መስማማቷ ተገለጸ

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሦስት ቢሊዮን ዳላር በኢትዮጵያ ለማፍሰስ መስማማቷ ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በኢትዮጵያ ፈሰስ ለማድረግ የሦስት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ስምምነት ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በብሔራዊ ቤተ-መንግስት መፈራረማቸው ተገልጿል።

 ከስምምነታቸው መካከልም አንድ ቢሊዮን ዶላሩ ኢትዮጵያ ላጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ጥያቄዎች ምላሽ እንደትሰጥ የሚያስችል ድጋፍ ስምምነት እንደሆነ ተገልጿል። ሁለት 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላሩ ደግሞ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባለሀብቶች በቀጥታ ኢንቨስትመንት የሚያፈሱት እንደሆነ ተመልክቷል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ እኩለ ቀን አዲስ አበባ የገቡትን  የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አልጋ ወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንን ከቦሌ አየር ማረፊያ ተቀብለው ራሳቸው መኪና እያሽከረከሩ ለጉብኝት ወደ ቦሌ ለሚ አይቲ (IT) ፓርክ  እንደወሰዷቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጿል።

በኢትዮጵያ በተለይም ህዝባዊ አመፅ ከተቀጣጠለበት ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ የሆነ ውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠማት ይታወቃል።

LEAVE A REPLY