ጅቡቲ ለ45 ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ምህረት ማድረጓ ተገለጸ

ጅቡቲ ለ45 ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ምህረት ማድረጓ ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጅቡቲ ለ45 ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ምህረት ማድረጓ ተገለጸ። የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡማር ጊሌ በተለያዩ ወንጀል ተከሰው ከ አንድ እሰከ 10 ዓመት ተፈርደባቸው በጅቡቲ ማረሚያ ቤት ለነበሩ 45 ኢትዮጵያዊያን ምህረት ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ፕሬዚዳንቱ ለእስረኞች ምህረት ያደረጉትም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጅቡቲ መጎብኘታቸውንና የረማዳን በዓል ምክንያት በማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።ከእስር የተፈቱት ኢትዮጵያዊያንም አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ ካማሉ በሗላ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱ ተነግሯል።

ዶክተር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑና የተለያዩ ሀገራትን ሲጎበኙ በባዕድ ሀገር ታስረው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ሲያስፈቱ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን በሱዳን ከአንድ ሽህ አራት መቶ በላይ ፣በኬንያ ከሁለት ሺህ በላይ፣በሳዑዲ አረቢያ ከአንድ ሺህ በላይ፣በኳታር ከሁለት መቶ በላይ እንዲሁም በግብፅ 32 እስረኞችን ማስፈታታቸው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY