/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማትን ለውጥ(ሪፎርም) ለማድረግ እየተደረጉ ባሉ እንቅስቃሴዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኃላፊዎች በአዳዲስ አመራሮች እንዲተኩ መወሰኑን ተከትሎ ዶክተር ይናገር ደሴ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ሆነው መሾማቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ዶክተር ይናገር ደሴ የብሔራዊ ባንኩ ገዥ የሆኑት ባለፉት 13 ዓመታት ሲመሩት የቆዩትን አቶ ተክለወልድ አጥናፉን በመተካት ነው። አቶ ተክለወልድ አጥማፉ ባንኩን ለ13 ዓመታት በመሩበት ወቅት በስርዓቱ ባለስልጣናት ከ30 ቢሊየን ዶላር በላይ ተመዝብሮ ከሀገር እንዲወጣ እድል መስጠታቸው ሲነገር ቆይቷል።
ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ባለፉት 27 ዓመታት በህወሓት ብቻ በበላይነት ሲመሩ የቆዩትን ተቋማት እየነጠቁ ሁሉንም ወገኖች ለማሳተፍ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል።