ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ በዚህ ማስታዋሻ ውስጥ ሁለት ትችቶች አሉ፡፡
የመጀመሪያው እና “አጭሩ“ (ቢያንስ እንዲህ እያልኩ የምጠራው አስተያየት ከዚህ በታች ) የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ክልል ውስጥ በመስጠት ላይ ስላለው አመራር የቀረበ ትችት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያውያንን ከበርካታ ሀገሮች ከእስራት እና ከእስር ቤቶች በማውጣት እያደረጉት ስላለው ህይወት አድን ልዩ ስራ አድናቆቴን የገለጽኩበት የተለመደው ማስታዋሻ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሚያዝያ መጀመሪያ ገና ስራቸውን ሲጀምሩ አዎንታዊ ድምጸቴን ከፍ አድርጌ በማሰማት ኢትዮጵያ ከጨለማው የጎሳ አፓርታይድ አዘቅት ውስጥ በመውጣት ረዥሙን ጉዞ በማድረግ አስራ ሶስት ወራት የጸሐይ ብርሀን የሚያንጸባርቅባት ምድር እንድትሆን ስማጸን ቆይቻለሁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ስራቸውን ከጀመሩ ጀምሮ ለበርካታ ዓመታት ስተነብየው የቆየሁት ጉዳይ በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ህወሀትን ሙሉ በሙሉ እርግፍ አድርጌ በመተው ወደ ታሪክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ጥየዋለሁ፡፡
ከዚህ በታች በአጭሩ እንደተመለከተው ኢትዮጵያን የእነርሱ ብቻ ለማድረግ የማይችሉ ከሆነ ኢትዮጵያን የመበታተን እና ፍጹም የሆነ የማውደም ዕቅዳቸውን በመሞከር የመጨረሻውን የምጽአት ቀን እውን ለማድረግ ህወሀት የህጻንነት አይነት ባህሪ ያለው መሆኑን፣ አጭበርባሪ፣ በጥባጭ፣ እርባናቢስ ባህሪ ያለው እና ኢሞራላዊ የሆኑ ተግባራትን የሚፈጽም መሆኑን በመጥቀስ ጥቂት ያለፉ ምልከታዎችን ለማቅረብ ዓላማ አድርጊያለሁ፡፡ የእነርሱ የምጽአት ቀን ዕቅድ እንዲህ ባለችዋ እንስሳ የአማርኛ የቀድሞ አባባል ይገለጻል፣ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል“
=============
ልዩ የሆነ ጠቃሚ ትችት፣
“ህወሀት ተጠንቀቅ በሰዎች ላይ እንዲፈጸም ስትመ
እ.ኤ.አ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓም ባቀረብኩት ትችት እንዲህ በማለት ጽፌ ነበር፣ “በአሁኑ ጊዜ ጂኒውከጠርሙሱ ወጥቷል፡፡
ለእነዚህ የህጻናት ዓይነት ባህሪ ለሚያሳዩት የህወሓት መሪዎች እውነቱን ልንገራቸው ምክንያቱም ንጹሀን ዜጎችን በመግደል፣ በማሰር እና በማሰቃየት ፍጎታቸውን ሊያሳኩ እንደማይችሉ እና በማጭበርበር የተገኘ ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ ሊጠቀሙ እንደማይችሉ እንዲሁም በየቦታው ያሉ በእራሳቸው የማይተማመኑ ቦቅቧቃ ፈሪዎች ልብ ገዝተው ድምፃቸዉን ከፍ አድርገው ስለህውሃት ወንጀሎች እንዲናገሩ ልብ ለመስጠትም ነው።
የሚገርም ነገር ነው! የቆሰለ አውሬ ለበለጠ በቀል ተመልሶ ለመምጣት በመጨረሻው የጣዕረሞት ትግል በመወራጨት ላይ ይገኛል፡፡ ህወሀት ከስልጣን መወገዱን ያህል የሚያስደስት ነገር የለም!
የህወሀት የምጽአት ቀን ዕቅድ በከፍተኛ ደረጃ ተጠናክሮ ይገኛል፡፡
ህወሀት ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲያራምደው የቆየውን ኢትዮጵያን ፍጹም በሆነ መልኩ ለማጥፋት እና የትግራይ ሪፐብሊክን ለመመስረት ሲያልም የቆየውን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የህጻንነት ባህሪውን ለዓለም በማሳት ላይ ይገኛል፡፡
ላፉት ጥቂት ዓመታት የህወሀት ዋና መሪዎች ኢትዮጵያን እንደ ብረት ቀጥቅጠው እንደ ሰም አቅልጠው መግዛት የማይሳካላቸው ከሆነ እና የጎሳ አፓርታይድ ስርዓታቸውን ለዘላለም ማስቀጠል የማይችሉ ከሆነ የትግራይ ሬፐብሊክ ምስረታ የምጽአት ቀን ዕቅዳቸውን ተግባራዊ ያደርጋሉ በማለት ፍንጭ እና ምልክት ሰጥተዋል፡፡ ዋናው መሮኋቸው “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቅል” ካለችው እንስሳ የቀድሞ አባባል ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ በሌላ አባባል ከእኔ በኋላ ጎርፍ በመምጣት ሁሉንም ነገር ይጠራርገው እንደማለት ነው፡፡
የትግራይ ሬፐብሊክን የመመስረት የህወሀት የምጸአት ቀን ዕቅድ ለበርካታ ዓመታት ታውቋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም የቀድሞው የህወሀት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት ገብረ መድህን አርዓያ የህወሀት ርዕይ እና ተልኮ ሁልጊዜ ትግራይን ከአማራ የቅኝ አገዛዝ ነጻ ማውጣት እና የትግራይ ሬፐብሊክን መመስረት እንደሆነ ግልጽ አድርገዋል፡፡ [የህወሀትን ዋናውን እና የመጀመሪያውን የእጅ ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ጋ ይጫኑ፣ ለግንኙነት መስመር ደግሞ እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት በማስረጃ በማስደገፍ እንዳቀረብኩት “የህወሀት መልዕክት ኢትዮጵያን ለዘላለም እንደ ብረት ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ መግዛት አለያም ደግሞ በቁንጮ ባለስልጣናቱ አማካይነት ሁልጊዜ በተደጋጋሚ ድፍረት የተቀላቀለበት ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት፣ ንግግሮችን ማድረግ እና ቅጥ አምባሩ የጠፋበት የጽሁፍ ትችቶችን ማቅረብ ነው”፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 2016 ዓ.ም የህወሀት ዋና አለቃ በኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሀሳባዊ የሆነ የዘር እልቂት እንደሚመጣ አወጀ፡፡ ዋና መልዕክቱም እንዲህ የሚል ነበር፣ “የሩዋንዳው ዓይነት በኢትዮጵያእንዳይደገ
ባለፉት ሁለት ዓመታት ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ የእርሱን የቅጥረኛ ኮማንድ ፖስት በማዋቀር እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ በኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር አገዛዙን በማስፋት የሞት የሽረት ትግል በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
መልዕክቱም እንዲህ የሚል ነው፣ “ህወሀት የሽብር አገዛዙን በህዝብ ጫንቃ
እ.ኤ.አ የካቲት 2018 ዓ.ም የህወሀት ዋና አለቃ ስዩም መስፍን የትግራይ ህዝብ የጦር ትጥቅ እንዲታጠቅ እንዲህ በማለት ጥሪ አቀረበ፣ “ጓዶች በአሁኑ ወቅት ተጋፍጠነው የሚገ
እ.ኤ.አ የካቲት 2018 ዓ.ም የህወሀት ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ኪዳን የህወሀትን ህልውና ለማረጋገጥ “ነጻ ኮሚሽን” እንዲቋቋም በማለት ድፍረት የተቀላቀለበት የተስፋ ድምጹን ከፍ አድርጎ በመናገር የህወሀትን የጎሳ አፓርታይድ ስርዓት ለማስቀጠል እና በአትዮጵያ ውስጥ የእርሱን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቡድን የበላይነት ዘላለማዊ ለማድረግ የሸፍጥ ዕቅዱን አቅርቧል፡፡
መልዕክቱም እንዲህ የሚል ነው፣ “ህወሀትን በስልጣን ላይ ለማቆየት የሚያስ
በአሁኑ ጊዜ ህወሀት ለማሸበር እና ለማስፈራራት እንዲህ በማለት ወኪሎቹን ይጠቀማል፡፡ “የትግራይ ህዝብየመዋጋት እና ድል
በአሁኑ ጊዜ ህወሀት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን መንግስት ለማዳከም በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የጎሳ ጥቃት እና የጥላቻ ችግር በመፍጠር ላይ ነው፡፡ መልዕክቱም እንዲህ የሚል ነው፣ “ህወሀት እንደፈለገው ሊያደርጋትየሚችለውን
በአሁኑ ጊዜ ህወሀት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ አሳሪውን የድንበር ኮሚሽን የስምምነት ውሳኔን ለይስሙላ በመቀበል (ከሟቹ ባለራእዩ መሪያቸው ከመለስ ዜናዊ በስተቀር ማንም ለመቀበል ያልተስማማበትን) ችግር ለመፍጠር በትግራይ ውስጥ ወጥነት የሌላቸው እና ከተለመደው ዓይነት ስርዓት ያፈነገጡ በሁለት ወይም በሶስት ቦታዎች ላይ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በማደራጀት ላይ ይገኛል፡፡ መልዕክቱም እንዲህ የሚል ነው፣ “ህወሀት የትግራይ ሬፐብሊክን ለመመስረት
ሁሉም የህወሀት የተፈበረኩ የማታለያ ዘዴዎች የዘላለም ህልማቸው የሆነውን የትግራይ ሬፐብሊክን ለመመስረት ከሆነ ጫካውን አትደብድቡ እላችኋለሁ (እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ እና 80ዎቹ ስታደርጉት እንደነበረው):: እስቲ ተነሱ እና በጭንቅላታችሁ ውስጥ ያለዉን ፍርጥርጥ አርጋችሁ ተናገሩ ። ማወናበዳችሁን አቁሙ፡፡
ሆኖም ግን ከ1994ቱ ትምህርት ውሰዱ፡፡ እንደፈለጋችሁ ለመፐወዝ ለምትሞክሩት እና ፍጹም የማይፈልገውን ምርጫ እንዲቀበል ለምታስገድዱት የትግራይ ህዝብ ታማኝ ሁኑ፡፡ እንዲህ የሚለውን አንድ እና አንድ ጥያቄ በማንሳት እራሳችሁን ጠይቁ፣ “እ.ኤ.አ በ1994 ዓ.ም ከኢትዮጵያ የ
የትግራይ ህዝብ ከቀሩት ኢትዮጵያውያን ወንደሞቹ እና እህቶቹ ጋር በሰላም እና በፍቅር መኖር ይፈልጋል፡፡ ከኢትዮጵያ መለየት/መገንጠል አይፈልጉም ምክንያቱም ትግራይ የኢትዮጵያ የመሰረት ድንጋይ ናት፡፡ በእኔ አመለካከት የትግራይ ህዝብ በአርበኝነት ተጋድሏቸው ወይም ደግሞ በኢትዮጵያዊነት ባላቸው ኩራት ከማንም በላይ ናቸው፡፡ ለዚህ አባባሌ ታሪክ ለማስተባበል የማይችለው ምስክር ነው!
እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን የትግራይ ህዝቦች ከማንም በላይ ያውቃሉ፡፡ ህወሀት በእነርሱ ስም እየነገደ እና የፍርኃት ጥላቻን እየቀፈቀፈ እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ የትግራይ ህዝቦች ህወሀት ስልጣን ላይ ተጠብቆ ለመኖር መጠቀሚያ እንደሆኑ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ የትግራይ ህዝቦች እስቲ ነጻ ሆነው መብቶቻቸው ይጠበቁ እና የምርጫ ድምጾቻቸውን በትክክል ለህወሀት ድጋፍ መስጠት አለመስጠታቸውን ውጤቶቻቸውን እንይ፡፡
ያም ሆነ ይህ የትግራይ ህዝቦች ባለፉት 27 ዓመታት ከሕግ አግባብ ውጫ ተስተናግደው ከሆነ እና መብቶቻቸው ተደፍጥጠው ከሆነ ይህንን የመብት ድፍጠጣ እና ከሕግ አግባብ ውጭ ማስተናገድን የፈጠረውን መንግስት እየተቆጣጠረ ያለው ማን ነው?
የህወሀት አመራሮች ያዘጋጃችሁት የምጽአት ቀን ሌላ በማንም ላይ ሳይሆን ዕቅዱ በእራሳችሁ ላይ እንደሚፈጸም እወቁ፡፡
የአንቀጽ 39 መርዝ ኢትዮጵያን አይገድላትም፡፡ ሆኖም ግን ኢትዮጵያን ይገድላል በማለት አስበው የዋጡትን ይገድላል፡፡
የህወሀት አለቆች የቀብር ደወሉ ለኢትዮጵያ ህዝቦች እየተደወለ ነው ብለው ያስባሉ፡፡
ስማ፣ ስማ፣ ህወሀት! “ደወሉ ለማን እንደተደወለ አላወቅኸውም፤የተደወለው ለአንተው ለእራሰህ ነው፡፡“
ህወሀት የተሻለ መንገድ አለ፡፡ ቀሪዎቹን ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችሁን እና አህቶቻችሁን ተቀላቀሉ እና እጅ ለእጅ በመያያዝ የአፍሪካን አህጉር የሚያቋርጡትን እና በኔልሰን ማንዴላ መልካም ነገር እና ይቅርባይነት እየተባሉ የሚጠሩትን ሁለቱን አውራ መንገዶች በማቋረጥ ተራመዱ፡፡
ተለዋጩ መንገድ ግን ወደ ሲኦል የሚወስደው መንገድ ነው፡፡
ለዚህም ነው እንግዲህ በሰዎች ላይ እንዲሆን ለምትመኙት ነገር ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባችሁ ምክንያቱም ለሌሎች የተመኛችሁት በእራሳችሁ ላይ ሊፈጸም ይችላልና፡፡ እናም ወደ መልካም ነገር የሚያስሄደውን አንዱን መንገድ ያዙ፤ የሲኦል መንገድ መመለሻ የለውምና፡፡
============
አብይ አህመድ “ህይወት አድኑ” ጠቅላይ ሚኒስትር
በኢትዮጵያ ውስጥ አእምሮ ከሚያስበው በላይ በበለጠ መልኩ ፈጣን የሆነ ለውጥ በማምጣት ላይ በመሆናቸው የዓለም ፈጣን የሩጫ ርቀት ሪከርድ ባለቤት በሆነው እና በስም ዩሰይን ቦልት እየተባለ በሚጠራው አትሌት ስም በአሁኑ ጊዜ አብይ አህመድን “ጠቅላይ ሚኒስትር ቦልት“ እያሉ የሚጠሩ አሉ፡፡
“ከጠቅላይ ሚኒስትር ቦልት” ጋር ምንም ዓይነት ችግሮች የሉብኝም፡፡ ለእኔ “የኢትዮጵያ ህይወት አድኑ” ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡
ይኸ ጉዳይ እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ አጋማሽ የአሜሪካ የፊልም አስቂኝ ተዋንያን ከሆነው እና እንዲህ ከሚለው ከጎስትቡስተርስ የሙዚቃ ቅላጼ የጥሪ ምላሽ ጋር ይመሳሰላል፡ “በጎረቤትህ አንድ የተለየ አዲስ ነ
እንገዲህ! ደህና በግብጽ ሀገር ህገወጥ በሆነ መልኩ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ካሉ እና እጅግ በጣም ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ የሚሰቃዩ ከሆነ ማንን ትጠራለህ? አብይ አህመድን!
በሳውዲ አረቢያ ሀገር ህገወጥ በሆነ መልኩ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ካሉ እና እጅግ በጣም ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ የሚሰቃዩ ከሆነ ማንን ትጠራለህ? አብይ አህመድን!
በሱዳን ሀገር ህገወጥ በሆነ መልኩ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ካሉ እና እጅግ በጣም ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ የሚሰቃዩ ከሆነ ማንን ትጠራለህ? አብይ አህመድን!
በኬንያ ሀገር ህገወጥ በሆነ መልኩ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ካሉ እና እጅግ በጣም ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ የሚሰቃዩ ከሆነ ማንን ትጠራለህ? አብይ አህመድን!
እ.ኤ.አ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በሆስፒታል ውስጥ እራሱን ለማወቅ በማይችልበት ሁኔታ/ኮማ ተኝቶ በሚገኝ ኢትዮጵያዊ ህጻን እና የሀገሩ መንግስት የተረሳ ካለ ማንን ትጠራለህ? አብይ አህመድን!
ኢትዮጵያውያን በእራሳቸው ሀገር ህገወጥ በሆነ መልኩ ከህግ አግባብ ውጭ ታስረው፣ ከህግ አግባብ ውጭ መብቶቻቸው ተደፍጥጠው እና ስቃይ የሚፈጸምባቸው ከሆነ ማንን ትጠራለህ? አብይ አህመድን!
ወደ ግብጽ ሄደህ