የወላይታ ዞን አስተዳዳሪዎች ከሀላፊነታቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን ገለጹ

የወላይታ ዞን አስተዳዳሪዎች ከሀላፊነታቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን ገለጹ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በደቡብ ክልል የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ከሀላፊነት ለመልቀቅ መስማማታቸውን ዛሬ በፃፉት ደብዳቤ ገልጸዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ፣ም/ አስተዳዳሪ፣ የድርጅት ጽ/ቤት ሀላፊ፣ የገጠርና ከተማ ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥያቄ በፀጋ በመቀበል መወሰናቸውን ገልፀው፣ ነገር ግን የድርጅትና የመንግስትን አመራር ተከትሎ በቦታቸው ሰው እስኪተካ በሀላፊነት ቦታቸው እንደሚቆዩ ገልጸዋል።

በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ሰሞኑን የርስ በርስ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ችግሮች በተከሰቱባቸው ቦታዎች ትናንትና ከትናንት ወዲያ ዕረብ ከህዝብ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት የሲዳማ፣ወላይታ፣ ጉራጌና ቀቤና ዞን አመራሮች ራሳቸውን ከሀላፊነት እንዲያነሱ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY