ሁለቱ ዶክተሮች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊመለሱ ነው ተባለ

ሁለቱ ዶክተሮች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊመለሱ ነው ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀ-መንበር የሆኑት እንዲሁም  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለበርካት ዓመታት የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የነበሩት ዶክተር መረራ ጉዲና ከሦስት ዓመታት በሗላ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሊመለሱ መሆኑ ተገለጸ።

ዶክተር መረራ ጉዲና ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ የበላይ አካላት እንደወሰኑላቸውና የዩኒቨርሲቲው ፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት ክፍልም ውሳኔውን መቀበሉን ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲውን የቦርድ አባላት ውሳኔ እንደሚጠብቁና የእነርሱም ምላሽ አውንታዊ ይሆናል ብለው እንደሚጠብቁ ዶክተር መረራ ጨምረው ገልጸዋል።

ዶ/ር መረራ ጉዲና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም-አቀፍ ግኑኘነት ትምህርት ክፍል ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ሲያስተምሩ የቆዩ ሲሆን ከሦስት ዓመታት በፊት ባላቸው የፖለቲካ አመለካከት ምክንያት ብቻ ዩኒቨርሲቲው የስራ ውላቸውን አቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።

በሌላ በኩል የፍልስፍና ምሁሩና በመንግስት ላይ የሰላ ትችት በማቅረብ የሚታወቁት ዶከተር ዳኛቸው ሰሰፋም ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሳቸውን ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል። ዶክተር ዳኛቸው አሰፋም እንዲሁ በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ላለፉት ሦስት ዓመታት ከስራ ገበታቸው ተነስተው ቆይተዋል።

LEAVE A REPLY