ያልተሰሙ ጩኸቶች!! /አመልማል ደምሰው አንዳርጌ/

ያልተሰሙ ጩኸቶች!! /አመልማል ደምሰው አንዳርጌ/

በኢትዮጵያ 27 የህወሃትወያኔ የቅኝ ግዛት ዘመንያላለቀሱ ዜጎች ቢኖሩ የሥርዓቱተጠቃሚዎችና ህሌናቸውንየሸጡ  ሆድ አደር ካድሬዎችብቻ ናቸው፡፡ እንደ ህወሃትዘመን የኢትዮጵያ ሕዝብበአገሩ ላይም ሆነ በሰው አገርከእስሳና ከእቃ በታች ተቆጥሮየተዋረደበ  ከቶ በታሪክታይቶም ሆነ ተሰምቶይታወቅም፡፡ ህወሃቶች የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ቀመር የተለየ ስብዕና የተላበሱ እርጉሞች ናቸው፡፡
እንኳን ሌላውን ኢትዮጵያዊ «ወጣንበት» ያሉትን ማህበረሰብ ሳይቀር የተለየ ሀሳብ ያራምዳል ብለው የጠረጠሩትን ሁሉ እየገደሉ እጃቸውን በደም ሲያጥቡ የመጡ አረመኔዎች! ከሃዲዎች! ናቸው! ለኢትዮጵያ መቆረስና ለህዝቦቿ መጎሳቆልና ጥፋት የተፈጠሩአጥፊዎች ናቸው! አስረው፣ ገርፈው፣ አሰድደው፣ ገለው፣ ሰውረው….  በሰው ልጅ ስቃይ መከራና እንግልት የማይረኩየማይጠግቡ ጉዶች! እነዚህ የአገር ነቀርሳዎች የመከራ እጃቸውን አንስተው ያላንኳኩት ኢትዮጵያዊ ቤት ቢኖር ምናልባት ዘመዶቻቸውን ብቻ ይሆናል፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የህወሃት ዱላ አርፎበታል፡፡ የህወሃት ጨካኝ ዱላ ካረፈባቸው ኢትዮጵያዊያት እናቶችና ሚስቶች አንዷ ነኝ፡፡

ጊዜው ሚያዚያ 24 ቀን 1989 ዓ.ም ነበር፡፡ ባለቤቴ አቶ ሙሉ አምባው ፈረደ በጨካኞቹ የህወሃት አፋኝ ቡድኖች ታፍኖ ከተሰወረ እነሆ 21 ዓመት አለፈው፡፡ ከቤቱ ወጥቶ የማምሸትም ሆነ የማደር ልማድ ያልነበረው የ3 ልጆቼ አባት ሙሉ በወጣበት ሲቀር ያሳለፍኩት የስቃይ ሌሊት ከደረሰበት ሰው በቀር ከቶ ማንስ ረዳው ይችላል?! በወቅቱ ከደረሰብኝ ጭንቀት የተነሳሳላብድ የመቅረቴን ምስጢር ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ልጆቼ ያለ እናት አባት እንዳይቀሩ ፈጣሪ አስቦላቸው ነው እላለሁ፡፡

ሚያሲያ 25 ቀን 1989 ዓ.ም በጥዋት ተነስቼ የሄድኩት ወደ አንጋፋው የመምህራን ማህበር ጽ/ቤት ነበር፡፡ ጥብቅ ጓደኛው የነበረውን አሰፋ ማሩን ለማነጋገር፡፡ አሰፋ ጋር ተገናኘሁ፡፡ ዛሬም ድረስ በጆሮዬ በሚያቃጭለው መልካም አንደበቱ ብዙ መከረኝ፡፡ ረጋጋኝ፡፡ አጽናናኝ፡፡ ቀጥሎም ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች በደብዳቤም ሆነ በአካል እየቀረብኩ እንዳመለክት በአጽኖት ነገረኝ፡፡ የሚያሳዝነው ግን ሚያዚያ 30/1989 ዓ/ም አሰፋ ማሩ በፋሽስቱ ህወት ጥይት ተበላ፡፡

አሰፋን በድንገት አድብቶ መግደል–  ባለቤቴ ሙሉ ለ21 ዓመት ያህል ከቤተሰብ መሰወር የአስፈለገበት ምክንያት ለእኔ እስከዛሬ ድረስ ግልጽ አይደለም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው1989 ዓ/ም የህወሃትን መንግሥት ሊገለብጥ ወይም ሊቀናቀን የሚችል በህቡም ሆነ በግልጽ የተደራጀ ኃይል ወይም ድርጅት እንዳልነበር ይታወል፡፡ ወንጀል ሰርተው ወንጀለኞች ሆነው ቢገኙ እንኳን በፍድ ቤት መዳኘት ሲቻል አንድ መንግሥት ነኝ ከሚል ተቋም እንዲህ ያለ ሀላፊነት የጎደለው የማፊያ ሥራ መስራት ከቶ ምን ሊባል ይላልኢትዮጵያ እንድትጠፋ ኢትዮጵያዊ ካባችን ለማስወለቅ ገናከጥንስሱ አማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ የተነሳው ህወሃት የዘር ቀለኝነቱን እየተወጣብን መሆኑ ይሆን?

ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዛሬ በግልጽ ጮኸቴን አሰማለሁ! ለ21 ዓመት ብሶቴን እንዳልተነፍስ ታፍኜ ኖሬያለሁ! ይህ የአልተሰማ ጩኸት የእኔ ብቻ ሳይሆን የብዙ ሺህ ኢትዮጵያዊት ሚስቶች ጩኸት ነው!

የብዙ ኢትዮጵያዊያት እናቶች ጩኸት ነው!!

የብዙ ኢትዮጵያውያን ልጆች ጩኸት ነው!!

የብዙ እህቶች ጩት ነው!

የብዙ ወንድሞች ጩኸት ነው!

በትግራይ የጨለማ እስር ቤት ለ24 አመት የሚማቅቁትን የሊቁን የእደስራቸው አግማሴን 9 ቤተሰብ የሰቆቃ ሕይወት ለመገንዘብ ሰው መሆን ብቻ ይበቃል፡፡ የሊቁ ጉዳይ በመታወቁ እየተጮኸላቸው ነው፡፡

በአራቱም የአገሪቱ ማዕዘን እየታፈኑ ተወደው የት እንዳሉ ያልታወቁትንበየጨለማ ቤቱ የሚማቅቁትን ሞተው የትምየተጣሉትን አቤት! ባይ ያጡ በብዙ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንደግሞ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ልክ እኔ እንደሆንኩት ሁሉም በየጓዳ ሀዘኑን በአንጀቱ ቋጥሮ እ!! እያለ ለተቀመጠው ድምጽ እንሁነው፡፡ ወገኖቼ! ድምጽ ሁኑን፡፡ አብራችሁን ጩሁ!! ሞቶ መቅበር ቁርጥ አለው፡፡ ሞቶ ያልቀበሩት ሰው ሁኔታ ግን ያስጨንቃል፡

ሳቃያችን! ጭንቀታችን! ግፍና በደላችንይታያችሁ! ይሰማችሁ፡፡ በአንድ እጅ አይጨበጨብም፡፡ የአንድሰው ጩኸት አይሰማም፡፡ አብራችሁን ጩኹ!! ከኖሩም መኖራቸውን ከሞቱም መሞታቸውን እንወቅ፡፡

እኔ በራሴ ባላቤቴን ካማጣቴ በተጨማሪ ብዙ በደል ደርሶብኛል፡፡ ጩኸቴን እንዳላሰማ ተከልክያለሁ፡፡ ለህይወቴ እስክሰጋ ድረስ ክትትል ተደርጎብኛል፡፡ ለልጆቼ እንኳ በትክክልአባታቸው እንዴት እንደ ተሰወረ ለማስረዳት ተቸግሬ ነው የኖርኩት፡፡ ሰለ አባታቸው ምንም ነገር እንዳያነሱለጓደኞቻቸውም እንዳይነግሩ ሳስጠነቅቃቸው ነው የኖሩት፡፡በናፍቆት ከመሸማቀቃቸው በላይ የአባታቸውን ሁኔታ የማወቅና የመገንዘብ መብታቸውን ተነፍገው ነው ያደጉት፡፡ ይህን ያደረኩት በየጊዜው በሚደርስብኝ ጫናና ማስፈራሪያ ነበር፡፡ እኔ እንኳ በህይወት ኖሬ እነሱ ማደግና ራሳቸውን መቻልነበረባቸው፡፡ በየጊዜው የአባታቸውን ድንገት ከቤት ወጥቶመሰውር በየጊዜው እየነገርሁና እያወያየሁ ስቃያቸው ንባለመጋራቴ ሳሬ ክፉ የህሊና ወቀሳ አትርፎብናል፡፡ በልጆቼ ላይበፈጸምኩት የፍርሀት እቀባ እስከወዲያኛው ጸጸቱ አይለቀኝም፡፡ ለልጆችና ለቤተሰብ የማይራራው ህወሃት እኔንም እንዳያጠፋኝፈሪ ሆንኩ፡፡ ፍርሀት ግን ደጋግሞ ሲገለኝ ኖረ፡፡ ይህንን የታመቀ ብሶት ለመተንፈስ ይመስለኛል  በ2008 ዓ.ም «ያልተቋጨ ጉዞ» የሚለውን በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ መፍሀፌን በድፍረት ያሳተምኩት፡፡

አገራችን ለ27 ዓመት የተገዛችው ኢህአዴግ በሚሉት ድርጅት ስም በህወሃት ነው፡፡ ህወያት ደግሞ ለጭካኔው ቃላት የማይገኝለት ገዳይ አፋኝ ድርጅት ለመሆኑ በየግባር ያየነው ነው፡፡ በዘር ለያይቶ አባልቶናል፡፡ እኛም ጀርባችን አመቻችተን እንዲጋልበን ፈቅደንለታል፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ከተመረጡ ወዲህ ግን (ድርጅቱ ያው ኢህአዴግ የሚሉት ቢሆንም) ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል እየሰነቅን እንገለን፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ በተለይ ከ40 ዓመት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን የሚያከብር መሪ አይተናል፡፡ ሰለፍቅርና ይቅር ሰለመባባል የሚሰብክ መሪ አግኝተናል፡፡ ሰለ መተባበር ጠቃሚነት የሚያመክት የሰለጠነ አስተሳሰብ ያለው መሪ ሰጥቶናል፡፡ መወያየት የችግሮች ሁሉ መፍትሄ መሆኑን የሚሰብክ ሀላፊነት የሚሰማው ለ21ኛው ምዕተ ዓመት አስተሳሰብ የሚመጥን ወጣት መሪ ኢትዮጵያ ጥቷታል፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ ጠመንጃ እንደማይጠቅምና በአገሩ ጉዳይ ላይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ለውይይት መቅረብ እንዳለበት አምኖ ለማሳመን የሚጥር መሪ አግኝተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ምድር በፖለቲካ አቋምም ሆነ በማንውም ነገር ሰው በአገሩ ላይ ተማቆና ፈርቶ መኖር እንደሌለበት አስምሮበታል፡፡ ይህንን እድል በመጠቀም እኔም ለ21 ዓመት አፍኜ ይው የኖርኩትን ብሶቴን የማሰማበት ጊዜው አሁን እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ለ21 ዓመት ያልተሰማ ጩኸቴ ኢትዮጵያዊ ወገኔ ሁሉ እንዲሰማውና አብሮኝ እንዲጮህ ጥሪዬን ከአክብሮት ጋር አቀርባለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚም ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ ለዚህ ዓይነቱ አቤቱታ መልስ እንደሚሰጡ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ይህ ጩኸት የእኔ ብቻ ሳይሆን የብዙ ኢትዮጵያውያት እናቶች፣አባቶች፣ሚስቶች፣ልጆች፣እህቶች፣ወንድሞች ጩኸት ነው!!

ሰውን አፍኖ በመሰወር ቤተሰብን ማሸማቀቅና መበደል በእኔና መሰሎቼ ያብቃ!!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ!!

amelmad@gmail.com

LEAVE A REPLY