/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ዶ/ር አብይ ነገ ቅዳሜ በሚካሄደው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ በመስቀል አደባባይ እንደሚገኙ እና ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ያለ ካድሬዎች ውትወታ በራሳቸው ተነሳሽነት በተሰበሰቡ ግለሰቦች በተጠራ ህዝባዊ ሰልፍ ላይ መሪ ተገኝቶ ንግግር የሚያደርጉበትን ይህንን ህዝባዊ ሰልፍ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እንደሚሳተፉበት ተገምቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቦታው ተገኝተው የሚያደርጉት ንግግር በተለይ በድርጅታቸው ኢህአዴግ ውስጥ ያለውን አለመረጋጋት እንደሚያስወግድ የሚገልፁ ተንታኞች መንግስታቸውንም የሚያጸና ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
በአንጻሩ ህዝባዊ ሰልፉ ወደአልተገባ አቅጣጫ እንዳያመራ ጥንቃቄ እንደሚሻ የሚሞክሩት እኒህ የኢትዮጵያ ነገ ድረገጽ የፖለቲካ አማካሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በተለይ የኢትዮጵያ ህዝብ ዋነኛ ጥያቄ የሆነውን የስር ነቀል ለውጥ ጥያቄ ተደራሽ የሚያደርጉበት አጋጣሚ ይሆናል ብለዋል።
በመቀጠልም ከአሁን በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጋቸው ንግግሮች የህዝቡን ልብ የመውረሳቸው ዋነኛ ምክንያት ላለፉት 27 ዓመታት በተቃዋሚዎች ሲጠይቁ የነበሩና ሕዝባዊነት ያላቸው ጥያቄዎች ተደራሽ ያደረጉ ንግግሮች መሆናቸውን ግንዛቤ ውስጥ በማካተት ነገ ቅዳሜ በሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የሚገዳደሯቸውን አካላት (የቀን ጅቦች) ፈተና ላይ የሚጥሉበት እንደሚሆን ግምታቸውን አስቀምጠዋል።