/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን የኤፈርት ንብረት የሆነው ፋና ራዲዮ ዘገበ።
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ከሦስት ወራት በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ወንበራቸውና ከዴኢህዴግ ሊ/መንበርነት መነሳታቸውን ተከትሎ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በህወሓት ረጅም እጅ በመታገዝ የዴኢህዴግ ሊ/መንበርነት መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ከሀላፊነት መነሳታቸው ተገልጿል።
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ሰሞኑን በሀዋሳ፣ወላይታ፣ወልቂጤና ሌሎች በርካታ ቦታዎች በተቀሰቀሰው ግጭት እጃቸው እንዳለበት የአካባቢው ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲገልጹ ነበር።
ሽፈራው ሽጉጤ የደቡንብ ክልል አስተዳዳሪ በነበረበት ወቅት የአማራን ህዝብ ከማፈናቀል ጀምሮ በርካታ ወንጀሎች እንደፈጸመ ይነገራል።
በሌብነት ከበሰበሱ ግንባር ቀደም የስርዓቱ ባለስልጣናት መካከልም ሽፈራው እንደሚጠቀስ ይታወቃል።ቀጥሎም እስካሁን በሰራቸው ወንጀሎች በህግ ይጠየቃል ተብሎ ይታሰባል።