ጠቅላይ ሚ/ትር አብይ አህመድ ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያዊያን ደም መለገሳቸው ተገለፀ

ጠቅላይ ሚ/ትር አብይ አህመድ ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያዊያን ደም መለገሳቸው ተገለፀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መስቀል አደባባይ በቦምብ ፍንዳታ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አጋርነት ለማሳየት በብሔራዊ ደም ባንክ ተገኝተው ደም መለገሳቸው የጠ/ሚኒስትር ጸ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ገልጸዋል፡፡

 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደም የለገሱት ለተጎጂዎች ያላቸውን ፍቅርና ህብረት ለመግለፅ መሆኑም ተገልጿል።ከዚህ ቀደምም ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች ተኝተው የሚገኙ ወገኖችንም ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ይታወሳል።

 በሌላ በኩል እስካሁን በፍንዳታው የሁለት ወጣቶች ህይወት ያለፈ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጎጂ ቤተሰቦችን በስልክ ማፅናናታቸው ታውቋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሆነው ነገር ሁሉ እጅግ እንዳዘኑና የሁሉም ተጎጂ ቤተሰቦች በቶሎ መፅናናትን ተመኝተዋል።

የወላይታ ሶዶ ተወላጁ ዮሴፍ አያሌው(28 ዓመት)እንዲሁም የጊምቢ ተወላጅ ጉሳ ጉዲሳ(25 ዓመት) እስካሁን ውድ ህይወታቸውን ካጡ ኢትዮጵያን መካከል ሲሆኑ የሁለቱም አስከሬን ቤተሰቦቻቸው ወደ ሚገኙበት የትውልድ ስፍራቸው በክብር እንደተሸኘ ተነግሯል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን አማን ዛሬ በትዉተር ገፃቸው እንደገለፁት፤እስካሁን ጉዳት ደርሶባቸው  ወደ ህክምና ተቋማት ከመጡት 156 ሰዎች መካከል  114 ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ 40 ሰዎች አሁንም  ደግሞ በሆስፒታል እየታከሙ ነው ብለዋል፡፡ሁለት ሰዎችም መሞታቸውንም ሚኒስትሩ ጨምረው ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY