ጠቅላይ ሚ/ትር አብይ አህመድ ከኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚ/ትር አብይ አህመድ ከኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተወያዩ ነው። አጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኪነ_ጥበብ ባህልን፣ ፍቅርን፣ ይቅርባይነትንና አብሮነትን ሊያጎለምስ እንደሚገባ አሳስበዋል። የኪነ_ጥበብ የእውነትና የፍትህ ጠበቃ መሆም አለበት ብለዋል፡፡ የኪነ_ጥበብ (አርቲስቶች) ባለሙያዎች የሀገራዊ ህይወታችንና እምቅ ሀብታችን በፈጠራ ፍንትው አድርጎ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል አርቲስት አስቴር በዳኔ ጠ/ሚኒስትሩ “ለኪነ_ጥበብ ባለሞያዎች በሚሰጡት ስልጠና ላይ ተጠርቼ ከገባሁ በኃላ በማላውቀው ምክንያት ከአዳራሹ እንድወጣ ተደርጌያለሁ፡፡” ስትል በፌስ ቡክ ገጿ ላይ ገልጻለች።

አርቲስት አስቴር በዳኔ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መድረኮች የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝን በተደጋጋሚ ስትተች ትታወቃለች።

LEAVE A REPLY