የመደመር ፖለቲካ /ገለታው ዘለቀ/

የመደመር ፖለቲካ /ገለታው ዘለቀ/

የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ በቅርቡባመጡት የመደመር ስሌት መሰረት ብዙ ኢትዮጵያዊይህን መርህ ወዶት መፈክር አድርጎት ይታያል። እኔምእንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረግየዴሞክራሲ ሽግግር ሂደት ራሴን ደምሪያለሁብያለሁ ታዲያ ዛሬ ይህን ጽሁፍ ሳዘጋጅ ስለዚህስለመደመር ጉዳይ ትንሽ ውይይት ለማንሳት አስቤነበር።

በርግጥ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ተደመሩሲሉ ጽንሰ ሃሳቡ ምን ምን ይዘት እንዳለው በጥልቀትሊያብራሩ የሚችሉት እሳቸው ራሳቸው ናቸው።እሳቸው በገባቸው ልክ እኔ ሊገባኝ ኣይችልም። ይሁንእንጂ እኔ ራሴን ስደምር የዚህ የመደመር ስሌትበጥልቀት እንዲገባኝና በዚያ መረዳት ላይ ሆኘ ድጋፌንእንድሰጥ ነው የምፈልገውና  መደመር ሲባልየገባኝን ጽንሰ ሃሳብ ዛሬ ለአንዳንድ ወገኖቼ ባካፍልጥሩ ይሆናል ብየ አሰብኩ። ይህ የጠቅላይ ሚንስትሩየመደመር መፈክር በርግጥ በኢትዮጵያ ውስጥመሰረታዊ የትርክት ለውጦችን (change of narrative) አንግቧል ወይ? የሚለውን መጠየቅ ተገቢ ነውና በዚህላይ እንወያይ።  

በሃገራችን ሁኔታ የመደመር ፖለቲካ በሚከተሉትመረዳቶች ላይ ቢመሰረት ለወደፊት የለውጥርምጃችን ሃይል ይሰጠናል ብየ አምናለሁ። ምን ጊዜምቢሆን ከግልብ መረዳትና ህዝባዊ ንቅናቄ ታቅበንበተሻለ የመረዳት ከፍታ ላይ ሆነን የምናደርገው ትግልነው ለውጥ የሚያመጣው። ባለፍንባቸው የህይወትልምዶቻችን ብዙ ግልጽነት የጎደላቸው መፈክሮችንስንከተል ኖረን ቆይተን  ዛሬ ላይ ሆነን ስናያቸ እንደመጨበጥ የሆኑ ነበሩና ማስተዋል ያስፈልጋልከሚል ነው። ወደ አነሳሁት ሃሳብ ልመለስናየመደመር ጽነሰ ሃሳብ ይዘቶች የሚከተሉት ሲሆኑበነዚህ ማማዎች ላይ ሆነን መደመርን ብንደግፍግሩም ይሆናል።

የመደመር (+) ማማዎች

1. ብዝሃነት

   መደመር ስንል ማቀፍን ወይም (inclusion) ያሳያል።መደመር ነጠላነትን (homogeneity) የሚያራምድወይም የሚያበረታታ ሳይሆን ተገጣጥሞ ሰፋ ያለመዋቅር መፍጠርን መያያዝን የሚያሳይ ጽንሰ ሃሳብነው። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ገዢ ኣሳብየነበረው ነጠላነትን( homogeneity) የሚያበረታታብሄሮች የራሴ የሚሉትን ግዛት እያጠሩየሚኖሩበትን ሁኔታ የሚያበረታታ ነበር። መደመር ግንይህንን የሚያፈርስ ነውና በርግጥ ጠቅላይ ሚንስትርአብይ ይህን ኣሳብ ሲያፈልቁ ሃገራችን ወደ ሌላየትብብር የመገጣጠም የህብረት ትርክት(narration) ውስጥ እየገባች እንደሆነ ያሳያልና ይህ የመደመርኣሳብ በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካውን ኣይዲዮሎጂናትርክት የሚለውጥ እንቅስቃሴ ሆኖ እናየዋለንየኢትዮጵያ ህዝብ የረጅም ጊዜ ጥያቄም ይህ ነበር።ቀድሞ የነበረው መደመርን የሚያኮስሰው የፖለቲካኣስተሳሰብ ብዙ ሰው ኣስኮርፎ የቆየ ሲሆን ዛሬየመደመር ፖለቲካ ሲመጣ ኢትዮጵያውያን ሁሉበግልም በቡድንም ተደምረናል! ተደምረናል! እያሉኣዲሱን ትርክት ሲደሰቱት በአንጻሩ ያለፈውን ትርክትአደባባይ ላይ ሲሰብሩት ይታያል።

በመሆኑም መደመርስንል እንግዲህ እኛ የተደመርን ሰዎች ይህንን መረዳትብናየው መልካም ነው። የመደመር ፖለቲካ በኢትዮጵያውስጥ የትርክት ለውጥ ያሳያል ስንል በተለይምበክልሎች ህገ መንግስታት ያለውን ኣንዳንድ ኣንቀጽየሚጻረር ኣስተሳሰብ ሆኖ ስለምናይ ነው። ይህ ክልልየነእገሌ ነው የሚለውን ትርክት ሽሮ ኢትዮጵያውያንበዋናው ቤታቸውም ይሁን በስቴቶቻቸው ተደምረውእንዲኖሩ የሚያደርግ በመሆኑ የብሄር ፌደራልስርዓቱን ራሱን የሚጋፋ ትርክት ይዞ እናያለን። የሃገራችን ሶሺዮ ፖለቲካ ጉዞ ወደ መለየት (separation) የመጣ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከፍ ብሎየመጣው የመደመር ጥሪ ይህንን የመለየት(separation) ፖለቲካ የሚጋፋ ሆኖ እናያለን። ይሄየሚደገፍ ትር ነውና ኢትዮጵያውያን ሁሉየመደመርን ጽንሰ ሃሳብ ከፍ አድርገው ሊይዙትይገባል።  

2. ክህሎትና እውቀት (skill & knowledge)

መደመር ማለት ማነባበር ማለት ኣይደለም። መደመርማለት የሚደመረው ነገር ተደምሮ የሚሰጠውን ዋጋ(value) ወይም እሴት በትክክል ማወቅና ማስላት መቻል ማለት ነው። የሚደመሩት ተለዋዋጮችተደምረው ያላቸውን የጋራ እሴት መረዳት ካልቻልንየመደመር ጽንሰሃሳ ገባን ማለት ኣይቻልም። ስለሆነምእንደመር ስንል ተደምረን የሚኖረን የጋራ እሴትእንዲሁም በኢኮኖ በማህበራዊ ጉዳይ፣በፖለቲካው መስክ የሚሰጠንን ትርፍ መተመን መቻልማለት ነው። የዶክተር አብይ የመደመር ኣሳብ ጥሩደጋፊ መሆናችን የሚለካው ተደምረን የምናገኘውንዋጋ ቀድመን ባሰላነው መጠን ነው። ስለዚህ ከኛከደጋፊዎች ይህንን የመደመር ዋጋ ኣስልቶ የማየትችሎታ ይጠይቀናል። ዋጋው በታየን መጠን ለትግሉየሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል እንችላለን። ከሁሉ በላይይህ ጽንሰ ሃሳብ አንድ ጊዜ ቦግ ብሎ የሚጠፋየስሜት ነገር ሳይሆን የኢትዮጵያውያን የአብሮነትመርህ በመሆኑ የመደመር ወይም የብዝሃነት ዋጋውበሚገባ ሊገባን ይገባል። ተደምሮ የመኖር ክህሎትንምልናዳብር ይገባል።

3. ጥምረት (Coalition)

ሌላው የመደመር ጽንሰሃሳብ የሚያመላክተው ነገርበተለይ ለተደራጁ የፖለቲካ ሃይላት የቅንጅት(Coalition) ወይም የመዋሃድ ጥሪ አለው። ሃገራችንወደ መቶ የሚጠጉ ፓርቲዎችን ይዛ ትወዛወዛለች።የአንድነት ሃይሎች ስለህብረት እያወሩ ነገር ግንኣይደመሩም። ኣንድ ኣይነት ኣይዲዮሎጂና ፖሊሲይዘው የተለያየ ፓርቲ ሆነው ይኖራሉ። አሁን ጊዜውየመደመር የቅንጅት ጊዜ ነው። የመደመር ጽንሰ ሃሳብለነዚህ ፓርቲዎች ትልቅ ጥሪ ኣለው። መሰባሰብመደመር ይጠበቅባቸዋል። የመድብለ ፓርቲ ስርዓትዋና ዓላማ ለህዝቡ ኣማራጭ ፖሊሲዎችን መፍጠርነው። ከመቶ በላይ ፓርቲ ቢኖረን ዚህን ፓርቲ ሁሉኣሳብ ለማወቅና ለመምረጥ ራሱን የቻለ የአንድ ኣመትኮርስ ሊወስድብን ይችላል። የፓርቲውን ስምሸምድደን ለመያዝም አንችልም። ፓርቲዎች ጠጋ ጠጋብለው ቅንጅት ፈጥረው ሁለትና ሶስት ሆነውለምርጫ ቢመጡ ልዩነቱን እየተመንን የተሻለውንለመምረጥ እንችላለን። ስለዚህ ይህ የመደመር ጥሪለነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ይሰራልና መደመርአለባቸው። በዶክተር አብይ የመደመር ስሌትም ይሄአሳብ የሚበረታታ ይመስለኛል። የተሻለ መድብለ ፓርቲስርዓት እንድንፈጥር ፓርቲዎች ብትደመሩ ከሁሉ በላይደግሞ መንግስትም ቢደግፋቸው  ተገቢ ነው።

4. ቅርጽ +

ሌላው የዚህ የመደመር ጽንሰ ሃሳብ ትምህርትሊሰጠን የሚችለው ነገር ከራሱ ከምልክቱየምንቀዳው ትምህርት ነው። የመደመር ምልክት (+) እንደሚያሳየው በአንድ የፖለቲካ መዋቅር ውስጥየሚኖሩ ዜጎችን ግንኙነት ያሳያል። ወደ ላይ ያለውመስመር በመንግስትና በህዝብ መካከል የጠበቀግንኙነትን የሚያሳይ ሲሆን ወደ ጎን ደግሞ ግለሰብከግለሰብ (interpersonal relationship) ቡድን ከቡድንእጅ ለእጅ መያያ ቃልኪዳን መግባ ያሳያል። ይህመስቀለኛ ምልክት የኢትዮጵያውያን አብሮ የመኖርየኪዳን ምልክት ሊሆን ይችላልና ይህንን ምልክትከመንግስታችን ጋር  ባለመተማመን የተቆረጠውንመስመር የምንቀጥልበት፣ መንግስታችን በኛ ምርጫየሚሾምበትና የሚሻርበት፣ ወደ ጎን እኛኢትዮጵያውያን ህብረት የምንፈጥርበት ብሄሮች፣ግለሰቦች በሙሉ ተደምረን የአንድ የፖለቲካናየኢኮኖሚ ህዝብ መሆናችንን የምናሳይበት ምልክትሊሆነን ይችላል። መተማመን ወደላይና ወደ ጎንየሚፈስበት የአብሮነታችን ምልክት ነው::

5. በግድ የሆነ ምስለት (Assimilation) ኣያሳይም

 በሂሳብ ጊዜ መደመር የሚከተለውን ጸባይያሳያል።

ለምሳሌ:-

6 ብርቱካን + 2 ብርቱካን = _________ተብሎ ቢጠየቅ

አንድ የአንደኛ ክፍል ተማሪ 8 ብርቱካኖች ይለናል። ልክነው። ነገር ግን ፖለቲካዊ መደመርን በዚህ ቀላልሎጂክ ናዘው ብንሞክር አይሄድልንም።  

ለምሳሌ:-

1 ሙዝ + 1 ፓፓያ + 1 ብርቱካን+ 1 ሎሚ =_____

ተብለን ብንጠየቅ ውጤቱን ለመናገር ትንሽ ማሰብሊጠይቅ ነው። ምን አልባትም ፣አንድ ሙዝ፣ አንድፓፓያ፣ አንድ ብርቱካን፣ አንድ ሎሚ ብለን ልንመልስእንችል ይሆናል። ነገር ግን እነዚህን ፍራፍሬዎችበአንድ ጠቅላላ ስያሜ ውስጥ ከከተትናቸውና ስንትፍረፍሬ አለ ከተባለ የተለያዩ ፍራፍሬዎች አሉን ልንልእንችላለን። ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ ትግሬዎች፣ጉራጌዎች፣ ወላይታዎች፣ አፋሮች ወዘተ ተደመሩሲባል አንድ ተደፍጥጦ የተፈጠረ ባህላዊ ቡድን ይሁኑማለት ኣይደለም። መደመር ማለት ልዩነቶቻችንእንዳሉ ሆነው ግን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚማህበረሰብ ኢትዮጵያዊ እንሁን ማለት ነው። ስለዚህመደመር ስንል በግድ የሆነ ምስለትን (assimilation) እናምጣ ሳይሆን ብዙህ ሆነን ግን በአንድ የጋራማንነት ስር ማለትም ኢትዮጵያዊነት ስር እንደር ማለትነው። በዚህ የመረዳት ማማ ላይ ሆነን መደመርንካየነው በርግጥ የሚደገፍ ኣሳብ ነው።

6. የዜሮ ድምር

በመደመር ጊዜ በውጤቱ ላይ ምንም ለውጥ ወይምእድገት የማያየው ዜሮን ጨምረን የደመርን እንደሆነነው። ዜሮ ባዶ በመሆኑ በድምራቸን ላይ ተጽእኖየለውም። የዶክተር አብይ የእንደመር ጥያቄ ለእኔየአስተዋጾ ጥያቄ ነው። ተጨባጭ የሆነ ተፈላጊለውጥ እናመጣ ዘንድ የለውጥ ሃይላት ሁሉየምንችለውን መወርመር አለብን። በሌሎች ዋጋተጨባጭ ለውጥን መናፈቅ ተደምሪያለሁ ከሚዜጋም ሆነ ቡድን አይጠበቅም። እኔ የዶክተር አብይየእንደመር ስሌት ደጋፊ ነኝ ብያለሁ ነገር ግንሁኔታውን እያየሁ የምደግፍ (conditional) ደጋፊ ነኝ።የመደመርን ኣሳብ እደግፋለሁ ስል የምደግፈውግለሰብን ሳይሆን ኣሳቡን ነው። በለውጡ ሂደትዶክተር ኣብይ ቢደክሙ ወይም ለውጡን ከዳርባያደርሱ ተደምሪያለሁ ብየ ሲያጠፉ ሁሉ ስደግፋቸውኣልኖርም። ይህ የመደመር ስሌት የመርህ ጉዳይ ነው።ሃገራችን ወደ ተሻለ የዴሞክራ ስርዓትየሚወስዳትን አመራር ሁሉ እየደገፍን የምንሄድበትመርህ እንጂ የግለሰብ ደጋፊ አይደለሁም። ስለሆነምለመደመር ጽንሰሃሳብ ሁኔታ የማያግደው(Unconditional) ደጋፊ ስሆን ለዶክተር አብይ ግን ሁኔታእያየሁ (Conditional) ደጋፊ መሆኔን ከአክብሮቴ ጋርእገልጽላቸዋለሁ። በርግጥ ግለሰቦች ባላቸውኣስተዋጾ ሊበረታቱ ሊደገፉ ይገባል። ነገር ግንየሙጥኝ ብለን የምንኖረው መርህን መሆን ኣለበት።ስለዚህ የመደመርን መርህ የምንከተለው ዶክተርኣብይ ስልጣን ላይ እስካሉ ብቻ ሳይሆን ሄደውም ይህንመርህ ስንደግፍ ልንኖር ይገባል። ለውጥ ምናመጣው ሁላችን አስተዋጾ ስናደርግ እሚደገፈውን ስንደግፍየማይሆነው ላይ ደግሞ እምቢኝ ብለን ስንታገል ነው። 

7. ምርኮ ማብዛት

Politics is about addition, not subtractionፖለቲካየመደመር እንጂ የመቀነስ ጉዳይ ኣይደለም። ይህንንአባባል መጀመሪያ ማን እንደተናገርው ኣይታወቅም።ነገር ግን እውነት ነው ፖለቲካ ስለመደመር ነው። ይህሲባል ጥላቻን፣ ወንጀልን ወዘተ መቀነስ ኣይገባምወይ? የሚል ቀላል ጥያቄ እንደማይነሳ እያሰብን ነው።ፖለቲካ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ጉዳይ፣ በፖለቲካጉዳይ መደመር ማደግን ዓላማው ኣድርጎ የሚሄድየአስተዳደር ጥበብ ነው። በሃ ልቀት በፖሊሲ ልቀትብዙዎችን እየማረከ የሚሄድ ጥበብ ነው። በሌላበኩል እንደመር የሚለው ቃል የፍቅር ጥሪ ነው።የብሄራዊ እርቅና መግባባት ጥሪ አለው። የማግለልየመቀነስ ባህርይ የለውም። ስለዚህ በመደመርትግላችን ወቅት ቡድኖችን የማግለል ስራ መስራትየለብንም። ምናገለውና የምናቅፈው ብለን የመለየትስራ መስራት የለብንም። በፍቅር የመማረ ስራመስራትን ይጠይቃል። ባለቅኔው ፍቅር ያሸንፋል!እንዳለው መደመር የፍቅርን የመቻቻልን ጥግየምናሳይበት ምልክት ነው በመሆኑም የዶክተርአብይን የመደመር የምንደግፈው ይቅርባይነትን፣መማረክን፣ በፍቅር ማሸነፍን ቀን መሆንይጠበቅብናል። የጥላቻ ፖለቲካ ከምድራችን ነቅሎይሄድ ዘንድ የመደመር ፖለቲካ በጣም ፍቱን መድሃኒትነው።

ስለዚህ ስለመደመር ፖለቲካ ብዙዎች ሲሉእየሰማን ነው። አንዳንዶች መደመር ሲባልየምንቀንሰውስ ኣለ ወይ? እነማን ይቀነሱ እነማንይደመሩ? ይላሉ። ማንንም አንቀንስም። ለመደመርነው የምንጥረው። ማንንም ለይተን ማንንምኣንቀንስም። ነገር ግን አንድነትን የማይሻ፣ የመለየትፖለቲካን የሚሻ ሰው እሱ በራሱ ኣይደመርም። ከዛውጭ ልበ ሰፊ ሆነን ሃገራችንን ወደ ተሻለ ስርዓትለመውሰድ የሚደመሩ የሚቀነሱ ብለን ኣንመድብም።በቻልነው ኣቅም ለመማረክ እየጣርን ከሄድን ነውየመደመር ፖለቲካ በጎ ፍሬ አፍርቶ የምናየው።በመሆኑም በፌስ ቡክ ይሁን በሌላ ሶሻል ሚዲያግለሰቦችንም ይሁን ቡድኖችን ይደመሩ ዘንድ ምርኮንመሰብሰብ ትልቅ ኣስተዋጾ ይሆናል። በመደመሩንቅናቄ ጊዜ አስመሳይ ኣድርባይ ይኖራል። ነገር ግንበሂደት ህዝባዊ ንቅናቄው አሸንፎ ስለሚወጣተጽእኖው ያን ያህል ኣስፈሪ ኣይሆንም።

8. ማባዛት፣ ማካፈልና መቀነስ

መደመርን ግባችን አድርገን ወደዚህ ግብ ለመድረስ መቀነስን ማባዛትን ማካፈልን ልንጠቀምባቸውእንደምንችል ማሰብ ለመደመር ስራችን ትልቅ ሃይልይሆነናል። አንዳንድ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ግንባታየማረዱ ጎታች የሆኑ አስተሳሶብችን መቀነስ እንደመደመር ይቆጠራል። ጥላቻን መቀነስ ፍቅርንመደመር ነውና። አለመተማመንን መቀነስ ማህበራዊ ሃብት ያድግ ዘንድ መደመር ነውና። ያለንን እውቀትማካፈል፣ አስተዋጾዎቻችንን ማብዛት መደመርነው በመሆኑም ለዶክተር አብይ የመደመር ጥሪመቀነስን፣ ማካፈልን፣ ማባዛትን ሁሉ መደመርአድርገን ልንጠቀምባቸው እንደምንችል ማስላትበተለይ ለተደረጁ ሃይላት ያስፈልጋል። ኣደገኛጉዳዮችን ሁሉ ወደ በጎ ለውጥ የመቀየር ችሎታመደመር ነው። ለውጣችንን የሚጎዱ ነገሮችንመቀነስ፣ መተማመን የሚጎዱ ጉዳዮችን መቀነስማለት ፖለቲካ ማለት መደመር ነው የሚለውንኣይጻረርም። ይልቁን መደመራችንን የሚያዳብርነውና።

9. የተቋማት መደመር

የዶክተር አብይ የተደመሩ ጥያቄ ለብሄሮችና ለዜጎችብቻ ሳይሆን በተለይ ለተቋማት ይመስለኛል። ፍርድቤት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ተደምሪያለሁ ማለት አለበት።ፖሊስ፣ ደህንነት፣ ወታደሩ፣ ባለሙያው ተማሪውአስተማሪው ተደምረናል የሚል ኪዳን ያስፈልጋቸዋል።ይህ የመደመር ንቅናቄ የፖለቲካ ርእዮት ሳይሆንኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ስርዓት ለማሻገርየሚደረግ ንቅናቄ በመሆኑ ተቋማት በተለይድጋፋቸውን ሊያሰሙ ይገባል። ይህ ነገር ለህዝቡ ትልቅተስፋና አቅም ይሆናል። ለለውጥ ሃይላትም ትልቅየሞራል ድጋፍን የሚሰጥ ይሆናል።

በመጨራሻም ዶክተር አብይንም ሆነ አብረዋቸውለለውጥ የሚታግሉ እንደነ ኦቦ ለማ መገርሳ ያሉየለውጥ ታጋዮችን ሁሉ ለጀመሩት ለዚህ የመደመርፖለቲካ እያመሰገንኩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ተግባራዊየሆኑ ለውጦች እንዲመጡ ሃገራችን ወደ ብሄራዊመግባባት እንድታልፍ እኛ ዜጎች ለመደመርናለመደመር ቆርጠን መነሳት አለብን። የለውጡሃይላትም ሃገሪቱን ወደ ተሻለ መድብለ ፓርቲ ስርዓትናምርጫ በአንድ ቃልም ወደ ሪፐብሊክ እንዲመሩእንደዜጋ እጠይቃለሁ። ሃገራችን ቀድሞ የነበራትዝናና ገናናነት ተመልሶ በእኛ ትውልድ የምናየውመደመርን መርህ አድርገን ስንታገል ነው።

 እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

         geletawzeleke@gmail.com

LEAVE A REPLY