የትግራይ ቴሌቪዥን ለብሮድካስት ባለስልጣን ምላሽ ሰጠ

የትግራይ ቴሌቪዥን ለብሮድካስት ባለስልጣን ምላሽ ሰጠ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የብሮድካስት ባለስልጣን  የትግራይ እና ENN የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በመስቀል አደባባይ ሰኔ 16/2010ዓ.ም የተካሄደውን የድጋፍ ሰልፍ ሽፋን ባለመስጠታቸው ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቃቸው የሚታወስ ሲሆን የትግራይ ቴሌቪዥን ዛሬ ለባለስልጣኑ ምላሽ ሰጥቷል።

የትግራይ ቴሌቪዥን ሰልፉን ለምን ሽፋን እንዳልሰጠው አራት ምክንያቶችን ጠቅሷል።

 ስለተካሄደው ሰልፍ ቀድሞ የደረሰን ጥቆማ ባለመኖሩ፤

ከሰኔ 16 ቀድሞ ሰኔ 15/2010ዓ.ም በትግራይ ክልል የሰማዕታት ቀን የሚከበርበት መሆኑ፤

E68DABB8-3272-4C34-9509-0C71A10E3F3B

የብሮድካስት ባለስልጣን ዜና ወይም ዝግጅት አለተካፈለም ብሎ ለመጠየቅ የሚያችል ህጋዊ ሀላፊነት እንደሌለውና ሌሎች ምክንያቶችን ለባለስጣኑ በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል።

በህወሓት ጄኔራሎች ከሁለት ዓመታት በፊት የተቋቋመው ኢ ኤን ኤን(ENN) የተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ እስካሁን በይፋ የሰጠው ምላሽ ባይኖርም የድርጅቱ ሰራተኞች እንደገለጹት ከሆነ ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ የቴሌቪዥን ጣቢያው መዘጋቱንና ሰራተኞቹንም እንደበተነ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY