/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የሰሜን ሱዳን ወታደሮች በመተማ በሚኖሩ ኢትዮጵያን ላይ ትናንትና ከትናንት በስቲያ በቀሰቀሱት ግጭት ከሁለቱም ወገን ሰዎች የሞቱ ሲሆን በደለሎ በኩል የሚገኘው የሱዳን ጦር ሀይል መደምሰሱን የአማራ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
አንድ የሱዳን ሻለቃ የጦር አመራርም ህይመቱ ማለፉ ተገልጿል።በቋራ ነብስ ገበያ በኩል በተፈጠረው ግጭት ደግሞ 7 የሱዳን ወታደሮች ሞተዋል፤ 2 መኪና እና 7 የጦር መሳሪያዎች መማረካቸው ታውቋል።
በኢትዮጵያ በኩልም ሦስት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እንዲሁም ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህይዎታቸዉ ማለፉንም ተረጋግጧል። ስድስት የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዉ ሆስፒታል መግባታቸው ታዉቋል፡፡ ከነዚህ መካከልም ሁለቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸዉ ተብሏል።
በሱዳን ጦር ሀይል ጥቃት ህይወታቸው ያለፈው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችና መከላከያ ሀይል አባላት አስከሬን አሁን ማምሻውን ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።