የሀዋሳ ከተማ ከንቲባና የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ከሀላፊነታቸው መልቀቃቸው ተገለጸ

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባና የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ከሀላፊነታቸው መልቀቃቸው ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከሁለት ሳምንታት በፊት በክልሉ የተፈጠረውን የርስ በርስ ግጭት ተከትሎ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባና የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ከሀላፊነታቸው ዛሬ መልቀቃቸው ተገልጿል።

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ እንዲሁም የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላ ሀላፊነታቸውን የለቀቁት በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች በተፈጠረው የርስ በርስ ግጭት በሰውና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማስከተሉ ሀላፊነት ለመውሰድ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

በደቡብ ክልል የተፈጠረው የጎሳ (ብሔር) ግጭት ተከትሎ በርካታ የደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች ሀላፊነት ለቀዋል። ሊ/መንበሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ጨምሮ ም/ሊ/መንበሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ የወላይታና የጉራጌ ዞን አመራሮች ከዚህ ቀደም ከሀላፊነት ቦታቸው መነሳታቸው ወይም መልቀቃቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ሰዓት ክልሉን እየመሩ ያሉት አቶ ደሴ ዳልጌም በቅርቡ የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እንደሚተኳቸው መገለፁ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY