/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የሞያሌ ከተማ ጉምሩክ ጣቢያ በደረሰበት የእሳት ቃጠሎ መውደሙን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ጠቆሙ።የኢትዮ_ሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ የጉምሩክ ጣቢያውን እንዳቃጠለውም እየተነገረ ነው።
ልዩ ፖሊሱ የጉምሩክ ጣቢያውን አቃጥለው ሲሄዱ የኢትጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀይል በአቅራቢያው የነበረና የተመለከተ ቢሆንም እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ ታውቋል።በቃጠሎውም በጣቢያው ውስጥ ተከማችተው የነበሩ የህዝብ ሀብትን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ተሽከርካሪዎች መውደማቸው ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ፖሊስ ከዚህ ቀደምም በሞያሌ፣ባሌ፣ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች ዘልቆ በመግባት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፅም መቆየቱ ይታወሳል።