የትግራይ ክልል ም/ፕሬዚዳንት ደብረጽዮን ገ/ማርያም ከትግራይ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች ጋር ትናንት ተወያዩባቸው የተባሉ ጉዳዮች ዝርዝር
የሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ዞሮ ዞሮ ከእኛ ጋር ነው የተሳሰረብን! ያፈነዱት ሰዎች ግን ይታወቃሉ! ቀድሞውኑም እንዲያ እንደሚያደርጉ ይታወቃል! ሆንተብሎ ወደ ትግራይ ማጣበቅ ነው የተሞከረው!! ከሰልፉ በኋላ ትግሬዎች ላይ ብዙ ፉከራ ነበር፤ ለማንኛውም መፍራት ሳይሆን መጠንቀቅ አለብን።
አሁን ባለው ሁኔታ መፍራትና መስጋት ተገቢ ቢሆንም፤ ይህን ስጋት ለበለጠ ትግል ማነሳሻ ልናደርገው ይገባል
ክልል ብቻ ሳይሆን ሀገርም ሊበተን ይችላል። ክልል የሚበተንበት ሁኔታ አሁን እየመጣ ነው። እኛ ግን እንደ ህዝብ አንድ እንሁን እንደራጅ፤ የትግራይን ህዝብ አንድነት ለመበተን እየተሰራ ስለሆነ…
3.800ሺ ጌድኦዎች በጉጂ ኦሮሞዎች ተባረዋል፤
የሀረሪ ብሄረሰብ እየተጨፈለቀ ነው
ወላይታ በገዛ ክልሉ ተባሯል፤ ትገድሏል
መሀል አገር ያለው ትግሬም ስጋት ላይ ነው! አንዳንዶቻችን እዚህ ሆነን “ዘራፍ!” እያልን መፎከራችን ጥሩ አይደለም! ትግሬው በመላ ኢትዮጵያ ነው ተበትኖ ያለው! አሁን እነሱን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር አናድርግ!! ለሁሉም ጊዜ አለው!!
እኛ የፌደራል ስልጣኑን እንዲሁ በግዴለሽነት አልተውንም፤ ቅድሚያ ትግራይ ላይ እናትኩር፤ ሀገርን (ኢትዮጵያን?) ደግሞ በ2ኛ ደረጃ አሥቀምጠን እንሥራ ብለን ነው። ይህ ደግሞ በወቅቱ ግርግር ምክንያት ሣይሆን፤ በመቀሌው ግምገማና አቅጣጫ መሠረት ነው
የትግራይን ወጣትና ምሁር እያስጠጋን እያሣተፍን ነው። አረናም ይሁን ማንም አብሮን መታገል ይችላል። የሃርመኒ ሆቴሉ የትግራይ ገቨርናንሥ ፎረም ይቀጥላል።
ኢሳያስ በሽታው አልተወውም፤ አሁንም “ወያኔ!” እያለ ነው ያለው፤ ስለ ድንበር አይደለም ያወራው
የትግራይን ህዝብ አንድነትና ጥቅም የሚጋፋ ታሪክን ወደ ኋላ ለመመለስ የሚጥር ሀይል አለ። አሁን በደምፍላት እርምጃ አንወሥድም፤ መጀመርያ የተደበላለቀው አሠላለፍ ይለይ። ወንጀላቸው ለጊዜው ይከመር በኋላ መጠየቃቸው አይቀርም።
(ትርጉም ምስጋናው አንዷለም)