አቶ ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት ድግሪ ተሰጡ

አቶ ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት ድግሪ ተሰጡ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጅማ ዩኒቨርሲ በ2010ዓ.ም በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎችን ዛሬ ሲያስመርቅ ለኦሮሚያ ክልል ር/መስተዳደር ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት ድግሪ መስጠቱ ተገልጿል። አጋፋው ጂማ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ለማ መገርሳ “የሰላምና ደህንነትየክብር ዶክትሬት ዲግሪ” መሆኑም ታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ለማ መገርሳ ባለፉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ በመደገፍ ከህወሓት ባለስልጣናት ጋር ከፍተኛ ትግል ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአፃራዊ መልኩ በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ለውጥ ለማምጣት የአቶ ለማና ቡድናቸው አስተዋዕፆ ቀላል አንዳልነበረ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ዛሬ ልዪ ስብሰባውን ያካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቦርድ አባላት ዶክተር መረራ ጉዲናን ጨምሮ ሌሎች አዳዲስ አባላትን መሾሙን አስታውቋል።

  የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አህመድ ሽዴን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን የቦርድ ሰብሳቢ፣ ዶክተር መረራ ጉዲና እና ወይዘሮ ሃሊማ ባድገባ አባል ሆነው እንዲያገለግሉ  መሾማቸው ታውቋል።

ዶክተር መረራ ጉዲና ለሁለት አስርት ዓመታት በማስተማር የቆዩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባላቸው የፖለቲካ አመለካከት ምክንያት ተባረው ለሦስት ዓመታት ያህል ከዩኒበርሲቲው ርቀው ቢቆዩም ባለፈው ወር ወደ ቀደመ ስራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ(ኦፌኮ) ሊ/መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ባለፈው የካቲት ወር የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል ሆነው መሾማቸውም ይታወቃል።

LEAVE A REPLY