/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ሰኔ 16 በመስቀል አደባባይ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው።ለጠቅላይ አብይ አህመድ ሰኔ 16/2010ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የተያዙ ተጠርጣሪዎች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ሌላ 11 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ ሌሎች ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት በሚል ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ለሐምሌ 13/2010 ዓ.ም ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ፍ/ቤቱ ሰጥቷል።
ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡ ተከሳሾች መካከል ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት አስተያየት “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥፋተኛ እንዳልሆንኩ ሲያውቁ ይቅርታ ይጠይቁኛል።”በማለት መናገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢንሳ) ም/ዳይሬክተር የነበረው ኮሎኔል ቢንያም ተወልደ ከሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ባለፈው ሳምንት በቁጥጥር ስር ውሎ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን እስካሁን ከ30 በላይ የሚሆኑ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነሮች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ይታወቃል።
Comment:አይ ኮምሽነር ግርማ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም። ሲባል አልሰሙም እስር እንዴት ነው? ደስ ይላል አይደል? ሃሃሃሃ…ሃሃሃ…ሃሃሃ…የናንተ ግን ትንሽ ወፌ ላላ የለውም።ገና በጭካኔህ ታስደስታቸው የነበሩት የበላይ ጀለሶችህ ይቀላቀሉሃል። አጁሃ